አዲስ አበባ | መስከረም 11 2016| NBC ETHIOPIA – የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይታቸው ወቅት ዋና ፀሐፊው ኢትዮጵያ በባለ ብዙ ወገን የትብብር ስርዓት ቁልፍ ሚና ያላት ሀገር ናት ብለዋል።
ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ጥልቅ የሆነ የአጋርነት ስሜት እንደነበራቸው ጠቅሰው ኢትዮጵያ ያሉባትን የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፈተናዎች ለመፍታት እያደረገች ባለው ጥረት ስኬታማ እንድትሆን ተመኝተዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ዋና ፀሐፊው በግል ጥረታቸው ለኢትዮጵያ በአስቸጋሪ ወቅቶች ላደረጉት ድጋፍ አመስግነው፣ የሰላም ስምምነቱን ትግበራ አስመልክቶ ገለጻ አድርገዋል።ተመድ የመልሶ ግንባታና መልሶ ማቋቋም ጥረቶችን እንዲሁም ሌሎች የሰብዓዊ ጉዳዮች ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በሌላ በኩል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከጉባኤው ጎን ለጎን ከኔዘርላንድስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃንክ ብሩዊንስ ጋር በሁለትዮሽ፣ቀጣናዊና የባለ ብዙ ወገን የትብብር ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
በውይይቱ ኔዘርላንድስ ኢትዮጵያ ለምታከናውናቸው የልማት ስራዎች የምታደርገውን ድጋፍ በተጠናከረ መልኩ እንደምትቀጥል የኔዘርላንድስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሃንክ ብሩዊንስ ገልጸዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram -https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












