አዲስ አበባ | መስከረም 8 2016| NBC ETHIOPIA- የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከካናዳ የአየር ትራንስፖርት ዋና ተደራዳሪ ሼንድራ ሜሊያ ጋር ተወያይተዋል።

ውይይታቸው ሁለቱ ሀገራት በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ላይ ያላቸውን ትብብር ማሳደግ የሚያስችሉ ዕድሎች ላይ ያተኮረ እንደነበር ተገልጿል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ካናዳ የሚያደርገውን የበረራ ቁጥር እንዲያሳድግ ዋና ተደራዳሪዋ መጠየቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
በዚሁ ጉዳይ ላይ ዕድሉን የበለጠ ማስፋት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ቀጣይ ውይይቶችን ለማድረግ መስማማታቸውንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ኢትዮጵያና ካናዳ ከግማሽ ምዕተ-ዓመት በላይ ያስቆጠረ ጠንካራ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ያላቸው አገራት መሆናቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram -https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት