አዲስ አበባ | መስከረም 8 2016| NBC ETHIOPIA- አቶ ደመቀ መኮንን ከቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ማርክ ሱዝማን ጋር በኒው ዮርክ ተወያይተዋል። በውይይቱ ኢትዮጵያ እና ፋውንዴሽኑ ያላቸውን ትብብር አድንቀዋል።

ኢትዮጵያ ከፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት በኋላ ሰላምን ለማጽናት እየሰራች እንደምትገኝና የ10 ዓመት የልማት እቅድ እየተገበረች መሆኑን ጠቅሰው ለዚህም አጋር አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
ኢትዮጵያ ጠንካራ የኢኮኖሚ እድገት በማስመዘግብ መቀጠሏንና እንደ አገር ፈተናዎችን መቋቋም የሚችል ጠንካራ አቅም መገንባቷን አመልክተዋል።
የስንዴ ምርት እና የሌማት ትሩፋት በሀገር ደረጃ ስኬት የተገኘባቸው ፕሮጀክቶች መሆናቸውንም ገልጸዋል።
ከልማት አጋሮች ጋር ያለውን ትብብር አበረታች መሆኑን ገልጸው፤ ኢትዮጵያ የጀመራቻቸውን መልካም ትስስር የመፍጠር ስራዎች አጠናክራ እንደምትቀጥል አመልክተዋል።
ማርክ ሱዝማን በበኩላቸው ፋውንዴሽኑ ከኢትዮጵያ ጋር በጤና፣ ግብርና፣ ዲጂታል ፋይናንስና ሌሎች መስኮች ጠንካራ ትብብር እንዳለው አንስተዋል።
ፋውንዴሽኑ ከኢትዮጵያ ጋር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑንና ከኢትዮጵያ የልማት መርሐ-ግብሮች ጋር በተጣጣመ መልኩ ያለውን ትብብር ይበልጥ እንደሚያጠናክር መናገራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram -https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት











