አዲስ አበባ | መስከረም 9 2016| NBC ETHIOPIA በክልሉ እየተካሄደ የሚገኘው አረንጓዴ አሻራ በምግብ ራሳችንን ለመቻል የምናደረገውን ጥረት የሚደግፍ ነው ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ገለጹ፡፡ በክልሉ እስካሁን አንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ችግኞች መተከላቸውን ጠቁመዋል፡፡

በአማራ ክልል በዘንድሮው ክረምት በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በተካሄደው የችግኝ ተከላ፤ ለደን ልማት ብቻ ሳይሆን ለምግብነትና ለፋብሪካ ጥሬ ዕቃነት የሚያገለግሉ ችግኞችን ጭምር በብዛት የተከልንበት ነው ብለዋል፡፡ ይህም በምግብ ራሳችንን ለመቻል የምናደርገውን ጥረት የሚደግፍ ነው ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram –https://t.me/nbcethiopiatv












