አዲስ አበባ | መስከረም 9 2016| NBC ETHIOPIA- የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ስብሰባ ተገኝተው ሩሲያ ዓለማችንን መጨረሻው ወደሌለው ጦርነት ከመክተቷ አስቀድሞ እንድትታቀብ ማድረግ ተገቢ ነው ሲሉ መናገራቸው ታውቋል፡፡

በአሜሪካ ኒው ዮርክ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት ስሜታዊነት የተቀላቀለበት ንግግር ያሰሙት ዜሌንስኪ፤ ኒውክሌር የታጠቀችው ሩሲያ ልትገታ ይገባል ብለዋል።
ሩሲያ በዓለም ላይ የምታመጣውን አደጋ በሚያመላክተው ንግግራቸው፤ እንደ አየር ንብረት ለውጥ ያሉ ጉዳዮችም ሊቀንሱ የሚችሉት ሞስኮ ስርዓት ስትይዝ ነው ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram –https://t.me/nbcethiopiatv












