፨ ፨ ፨ ፨ ፨፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 30 2016| NBC ETHIOPIA-ቻይና ለአፍሪካ አህጉር የምታደርገውን ድጋፍ ወደ 51 ቢሊዮን ዶላር ለማሳደግ ቃል እንደምትገባ ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ አስታወቁ።
ፕሬዝዳንት ሺ የቻይና-አፍሪካ የትብብር ጉባኤ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት የገንዘብ ድጋፉ ለተጨማሪ የመሠረተ ልማት ውጥኖች የሚውል ነው።
ቻይና ከአፍሪካ ጋር በኢንዱስትሪ፣በግብርና፣በመሰረተ ልማት፣በንግድ ፣ ጤና፣ መገናኛ አውታሮች ልማት፣አረንጓዴ ልማት ፤ደኅንነት እና በኢንቨስትመንት ትብብሯን ለማጠናከር መዘጋጀቷን ገልጸዋል።
እነዚህ መስኮች ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ከትብብር ማህቀፉ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ይጠበቃል።
ይህ የትብብር ማዕቀፍም በትንሹ በአህጉሪቱ ለሚገኙ 1 ሚሊዮን ዜጎች የስራ እድል እንደሚፈጥር ጠቁመዋል።የቻይና መንግስት በሚቀጥሉት ሶስት አመታት ውስጥ ለአፍሪካ ሃገራት የሚያደርገው የ51 ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍም፤ ለረዥም ጊዜ የቆየውን የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ መሆኑን ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ በቻይና እና አፍሪካ መካከል ያለው ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ሊሸጋገር እንደሚገባው ነው የጠቆሙት፡፡
በቻይናዋ ርዕሰ መዲና ቤጂንግ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የቻይና-አፍሪካ የትብብር ጉባኤ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ50 በላይ የአፍሪካ ሃገራት እየተሳተፉ ነው።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












