፨ ፨ ፨ ፨ ፨፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 30 2016| NBC ETHIOPIA- ከ112 አመታት በፊት የሰመጠችው ታይታኒክ መርከብ ወዳረፈችበት የውቅያኖስ ወለል በተደረገ ጉብኝት ግልጽ የመበስበስ ምልክቶች እያሳየች መሆኑ ታወቀ።
ለሁለት ተከፍላ የሰመጠችው 269 ሜትር ያህል ርዝመት የነበራት ይህች መርከብ ያረፈችው ከባህር ጠለል በታች 3.8 ኪሜ የሚርቅ የውቅያኖስ ወለል ላይ ሲሆን በአካባቢዋ ያለው ከፍተኛ የውሀ ግፊት፣ የውቅያኖሱ ሞገድ፣ እንዲሁም ብረት-በል ባክቴርያዎች እና ፈንገሶች እያፈራረሷት እንደሆነ ነው የተገለፀው ።

በዚህ ምክንያት በከፍተኛ ሁኔታ የዛገ እና የተበላ ሰውነት ያላት መርከቧ ቅርጿን ጠብቃ ለረጅም ጊዜ መቆየት እንደማትችል ነው የሚገመተው ዘገባው የቢቢሲ ነው።
በ-ዳንኤል መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












