፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 27 2016| NBC ETHIOPIA- 5ተኛው የአፍላ ወጣቶች እና ወጣቶች ጤና ጉባኤ በአድዋ ሙዚየም መታሰቢያ አዳራሽ እየተካሄደ ነው።
መድረኩ ተደራሽነት እና ጥራት ምላሽ ሰጪ የጤና ሥርዓት ለሁሉም የአፍላ ወጣቶች እና ወጣቶች በሚል መሪ ቃል እየተከናወነ ይገኛል።
የመርሐ ግብሩ ዓላማ በዋናነት የወጣቶች ጤና መጠበቅ እና አምራች ኃይልን ማሳደግ እንደሆነም ተመላክቷል።
በመርሐ ግብሩ የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር፣ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፣የሴቶች እና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ፣የዓለም የጤና ድርጅት ተወካይ የክልል የጤና ቢሮ ኃላፊዎች፣የጤናው ዘርፍ የሙያ ማሕበራት እና ወጣቶች ታድመውበታል።
በ-ፍቅረሚካኤል ዘየደ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












