፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 11 2016| NBC ETHIOPIA-በርካታ የቱሪስት መዳረሻ የሆኑ አገራት የቱሪስቶችን ፍሰት ለመጨመር ቅንጡ ሆቴሎችን ይገነባሉ፡፡ በሆቴሎቹ የሚደረጉ መስተንግዶዎችም ከመግቢያ አቀባበል ጀምሮ አንዳንዴ እንዲህም አለ እንዴ የሚያስብል ይሆናል።
ልዩ የፈጠራ ጥበብ የታከለባቸው ምግቦች በልዩ መስተንግዶአዊ አቀራረብ ለተጠቃሚዎች የሚያቀርበውን ታዋቂውን የዓለማችን ቅንጡ እና ውዱ ሬስቶራንት እናስተዋወቃችሁ።
ይህ የምትመለከቱት የምግብ አይነት ነው ቢባሉ ያምኑ ይሆን? በዚህ ሬስቶራንት ምግብ ምግብ ብቻ ሆኖ አይቀርብም ጥበብ ታክሎበት እንጂ።
ደግሞ ለምግብ ምን የሚሉት መጠበብ ነው ሊሉ ይችላሉ ነገር ግን ዲስፍሩታር ሬስቶራንት በሚያቀርባቸው አስገራሚ የምግብ ፈጠራዎቹ የፈረንጅቹ 2024 ምርጡ የዓለማችን ሬስቶራንት መሆን ችሏል።
ወደ ዲስፍሩታር ሬስቶራንት ጎራ ያሉ እንደሆነ በምግቡ ጣዕም ተማርከው ብቻ ሳይሆን በምግብ አሰራር ጥበቡም ተደምመው ይወጣሉ።
ዲስፍሩታር በስፔን ባርሴሎና የሚገኝ ከተለመደው የምግብ አሰራር ውጪ ለየት ያሉ አስገራሚ ፣እጅን በአፍ የሚያስጭኑ አንዳኔዴም ፈገግታን የሚጭሩ ምግቦችን የሚያገኙበት ቅንጡ ሬስቶራንት ነው።
ስፔን ጎራ ያሉ እንደሆነ ወደዚህ አስገራሚ ሬስቶራንት ሳያቀኑ መመልስ የማይታሰብ ስለመሆኑ እግራቸው ባ የረገጠ ሁሉ ይስማሙበታል። ዲስፍሩታር በስፓኒሽ “መደሰት” የሚል ትርጓሜን አለው።

ሬስቶራንቱ ይበልጡ የሚታወቀው ጣፋጭ ፣አስገራሚ እና ለየት ያሉ የምግብ አሰራሮችን ለተጠቃሚዎቹ በማቅረቡ ነው።
ቀደም ሲል በታዋቂው ኤልቡሊ ሬስቶራንት ውስጥ ይሠሩ በነበሩት በሼፍ ማትዩ ካሳናስ፣ ኦሪኦል ካስትሮ እና ኤድዋርድ ካትሩች እ.ኤ.አ. በ2014 ነው ዲስፍሩታር ሬስቶራንት የተከፈተው ።
በዲስፍሩታር ሬስቶራንት ሼፎች የምግብ አሰራር ጥበብን ብቻ ሳይሆን ፍጥነትንም ተክነውቦታል። ምግብ ዘገየ ብለው በፍጹም ስጋት አይገባዎትም ያዘዙት ምግብ በብርሀን ፍጥነት ያገኙታል።
ሬስቶራንቱ በዓለም ላይ ካሉ እጅግ ልዩ ፈጠራ የታከለበት ምግብ ከሚያቀርቡ ሬስቶራንቶች አንዱ ነው። ሬስቶራንቱ ያልተጠበቁ የጣዕም ቅንጅቶች ያሏቸውን አዳዲስ የምግብ አሰራር እና አቀራረብ ያሳያል።
የስፔን ባህላዊ የምግብ አሰራርን ከዘመናዊ በማቀናጀት የተለያዩ ቀለም እና ጣዕም ያላቸውን አዳዲስ የምግብ ፈጠራዎችን ያቀርባል።
ሬስቶራንቱ ከምርጥ ምግብ በተጨማሪ በሚያምር እና ዘመናዊ የመመገቢያ ክፍልም ፈጽሞ የሚታማ አይደለም ። እጅጉኑ ያማረ እና ትልቅ የመመገቢያ ክፍሎችም ያሉት ነው።
በ-ሀይማኖት ወርቁ












