፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 12 2016| NBC ETHIOPIA-በ2014 ዓ.ም በአማራ እና በአፋር ክልሎች በጦርነቱ ምክንያት ጾታዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች የሚውል ብር 45 ሚሊዮን 176,145.34 ስራ ላይ አለመዋሉ ተገልጿል፡፡
በ124 የመንግስት መስሪያ ቤቶች ከ14 ቢልዮን ብር በላይ በወቅቱ ያልተወራረደ ተሰብሳቢ ሂሳብ መገኘቱን የፌዴራል ዋና ኦዲተር አስታውቋል፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 32ኛ መደበኛ ስብሰባውን ባካሄደበት ወቅት የፌደራል ዋና ኦዲተር የ2015 በጀት ዓመት የፌደራል የመንግስት መስሪያ ቤቶች የፋይናንስ ህጋዊነት ኦዲትና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት አድምጧል።
በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በሴቶች እና ህጻናት ላይ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን በሚፈጽሙ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል የህግ ማእቀፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ተፈጻሚነቱን ሊከታተልና ሊቆጣጠር የሚገባ ቢሆንም የሚፈለገው ልክ እርምጃ ያልወሰደ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በ2014 ዓ.ም በአማራ እና በአፋር ክልሎች በጦርነቱ ምክንያት ጾታዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች የሚውል ብር 45,176,145.34 ስራ ላይ ያልዋለ መሆኑን የፌዴራል ዋና ኦዲተር በኦዲት ግኝት ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












