፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ12 2016| NBC ETHIOPIA-የፍትህ ሚኒስቴር ልዑክ ቡድን በሩሲያ ሴንት ፒተርስበርግ ከብሪክስ አባል ሃገራት ከሆኑ አቻ የአቃቤ ሕግ አመራሮች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት እያካሄደ ይገኛል፡፡
በሩሲያ ሴንት ፒተርስበርግ ከተማ የገባው በብሪክስ ሃገራት የአቃቤ ሕጎች ሐላፊዎች ስብሰባ ከሰኔ 10 እስከ 14/2016 ዲጃታል መፍትሔ ለወንጀል መከላከል እና የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል።

በስብሰባውም ላይ አቶ ተስፋዬ ዳባ የአቃቤ ሕግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ጨምሮ በአቃቤ ሕግ ዘርፍ የተደራጁ ወንጀሎች እና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ጉዳይ ጀነራል ዳይሬክተር አቶ ዮሲያድ አበጀ እና ወ/ት ሀና ግዛዉ የኢኮኖሚ ወንጀሎች ጉዳይ ጀነራል ዳይሬክተር እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በዚህም መሠረት የልዑክ ቡድኑ ከቻይና፣ ከተባበሩት አረብ ኢሚሬት ፣ከብራዚል እና ደቡብ አፍሪካ አቻዉ ጋር በሕግ ትብብር ፣ወንጀለኞችን እና የወንጀል ተጠርጣሪዎችን አሳልፎ መስጠት ፣የወንጀል ፍርደኞች ቅይይር ፣ ከአገር ተዘርፈዉ በሚሸሹ ሐብቶች ዙሪያ ላይ ገንቢ ዉይይት ያደረገ ሲሆን የተጀመሩ የስምምነት ድርድሮች እንዲፋጠኑ እና ተግባራዊ እንዲሆኑ መግባባት ላይ ተደርሷል። በዉይይቱም በፍትህ ዘርፍ የብሪክስ አገሮች ግንኙነት በሚጠናከርበት ሁኔታ በስፋት ዉይይት ተደርጓል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












