፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 12 2016| NBC ETHIOPIA- የ2016 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በ183 ጣቢያዎች መሰጠት መጀመሩን የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

ፈተናው ያለምንም እንከን እንዲጠናቀቅ በሁሉም የፈተና ጣቢያዎች የፈተና አስፈጻሚዎችን ጨምሮ በቂ የጸጥታ አካላት መመደባቸውን የቢሮው ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) አስታውቀዋል።
ተማሪዎች ለፈተናው ብቁ እንዲሆኑ የማጠናከሪያ ትምህርትን ጨምሮ ደረጃቸውን የሚመጥን ሞዴል ፈተና መሰጠቱን ጠቁመዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












