፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 11 2016| NBC ETHIOPIA- ምክር ቤቱ በ32ኛ መደበኛ ስብሰባው የፌዴራል ዋና ኦዲተር የፌዴራል መንግሥት መ/ቤቶች የ2015 በጀት ዓመት የፋይናንስና ሕጋዊነት ኦዲት እና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት እያዳመጠ ይገኛል።
ሪፖርቱን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ዋና ኦዲተር ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ እያቀረቡ ነው፡፡
ክብርት ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ በሪፖርታቸው እንዳብራሩት በ2014 በጀት ዓመት እና ከዚያ በፊት በተከናወኑ የኦዲት ሪፖርቶች መሠረት እርምጃ የተወሰደ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በገንዘብ ሚኒስቴር በ2014 በጀት አመት ተቀባይነት የሚያሳጣ አስተያየት ከተሰጣቸው 19 መ/ቤቶች እና የኦዲት አስተያየት መስጠት ካልተቻለባቸዉ 6 መ/ቤቶች ዉስጥ በ6 ዩኒቨርሲቲዎች እና በ7 መ/ቤቶች ላይ የገንዘብ ቅጣት እና ከባድ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ የተሰጠ መሆኑን በሪፖርታቸው ገልፀዋል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የ3 ዩኒቨርሲቲ ሃላፊዎች ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ መደረጉን በሪፖርቱ ተብራርቷል፡፡
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Website – https://nbcethiopia.com/news/
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












