፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 11 2016| NBC ETHIOPIA-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው በተለይም በኅብረተሰብ ልማት ፕሮጀክት የታቀፈ የሰብል ልማት፣ የአትክልትና ፍራፍሬ፣ የወተት፣ የዶሮ፣ የንብ ማነብ፣ የአሳ እርባታን ጎብኝተዋል።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በማዕድን፣ በለም አፈር፣ በመልካም የአየር ጠባይ የታደለ መሆኑን ያነሱት ምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህም ለክልሉ ትልቅ የመልማት አቅም ነው ብለዋል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በግብርና ሥራ ለውጥ ካመጡ ክልሎች አንዱ እንደሆነ በማንሳት÷ ተዘዋውረው የተመለከቷቸው የሌማት ትሩፋት ሥራዎች በአጭር ጊዜ አበረታች ውጤት ማምጣታቸውን ገልጸዋል።
የኸልዋ አግሮ ኢንዱስትሪ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ውጤታማ ሥራ መስራቱን ጠቅሰው÷ኢንዱስትሪው የኑሮ ውድነትን በማረጋጋትና በሥራ ዕድል ፈጠራ ለውጥ ያመጣ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
በጉብኝት መርሐ ግብሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን እና ሌሎች የሥራ ሃላፊዎችም ተገኝተዋል።
????YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
???? TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
????Website – https://nbcethiopia.com/news/
????Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












