፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 07 2016| NBC ETHIOPIA-ሞስኮ 87 የሚደርሱ የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትታ መጣሏን አስታውቃለች፡፡
ለጥቃት ከተላኩት ውስጥ 70 ሚሆኑት ሰው አልባ አውሮፕላኖች በደቡባዊ ሮስቶቭ ግዛት በሩሲያ ወታደራዊ ማዘዣ ማዕከል ላይ ኢላማቸውን ያደረጉ ነበሩ ተብሏል ፡፡

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፤ የኬይቭ ወታደሮች በሰው አልባ አውሮፕላን ታግዘው ሊፈፀሙት የነበረው የሽብር ጥቃት ከሽፋል ፡፡
በተያያዘ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሜር ዜለንስኪ ከአሜሪካ ጋር ለአስር ዓመት የሚቆይ ወታደራዊ ስምምነት አድርገዋል ፡፡ ይህን ተከትሎ ዜሌንስኪ በሁለቱ ሀገራት የተደረሰውን ስምምነት ታሪካዊ ቀን ብለውታል፡፡ ዘገባው የሞስኮ ታይምስ ነው፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv











