፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሰኔ 01 2016| NBC ETHIOPIA- ዩክሬን ከአሜሪካ በተሰጣት የጦር መሳሪያ በመታገዝ ሩሲያ ላይ ጥቃት ጀመርኩ ማለቷ ተሰምቷል ፡፡
ኬይቭ ባለፈው ሳምንት በከፈተችው ሁለት የመልሶ ማጥቃት እና መከላለከል እርምጃ ውጤታማ እንደሆነችም አስታውቃለች፡፡

በፈረንጆች ግንቦት 10፤ 2024 ሩሲያ በካራኪቭ ግዛት ጥቃት ማድረሷን ተከትሎ፤ ፈረንሳይና ጀርመን የጦር መሳሪያ ድጋፍ ለማድረግ ግንቦት 26 እና 27 ስምምነት ላይ ደርሰው እንደነበር ይታወሳል ፡፡
ይህንን ተከትሎ ዩክሬን ከአሜሪካና ምዕራባውያን በተደረገላት የጦር መሳሪያ ድጋፍ ሩሲያ ላይ ውጊያ መክፈቷ ተነግሯል ፡፡
ዩክሬን በሩሲያ ምድር ላይ ጦርነት መክፈቷን ብታውጅም ከክሬምሊን ባለስልጣናት ግን እስካሁን ድረስ የተሰጠ ማስተባበያ የለም ፡፡ ዘገባው የአልጀዚራ ነው፡፡
በ- ቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












