፡፡ ፡፡ ፡፡ ፡፡
አዲስ አበባ | የካቲት 19፣ 2016| NBC ETHIOPIA -ከ10 ዓመታት በላይ ተቋርጦ የቆየው ዓመታዊው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት ፌስቲቫል የፊታችን የካቲት 29 እንደሚመለስ ተነግሯል።
ፌስቲቫሉ ከየካቲት 29 ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በሁሉም ኮሌጆች መካከል በሚደረግ ውድድር በዋናው ግቢ እንደሚካሄድ የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ተናግረዋል።
በፌስቲቫሉ እግር ኳስ ፡ ቅርጫት ኳስ፡ ቮሊ ቦል፡ አትሌቲክስና ፓራላምፒክ የስፖርት አይነቶች መካተታቸውንና የስፖርት ማዘወተሪያ ስፍራዎች ዝግጅት እየተገባደደ መሆኑን አክለዋል።
በቀጣይ በሌሎችም ካምፓሶች ያሉ ማዘውተሪያዎችን በማደስ ላቅ ባለ ደረጃ ለማካሄድ ማቀዳቸውንም እንዲሁ።አላማው ማህበረሰባዊ ግንኙነቱን ከማጠናከር ባሻገር አገርን በተለያዩ መድረኮች የሚወክሉ ፕሮፌሽናል ስፖርተኞችን ማፍራት ነው ብለዋል።
አንጋፋው አዲስ አበቫ ዩኒቨርሲቲ ካለው መልካም ስምና ተጽዕኖ አኳያ ይህ ፌስቲቫል አገራዊ መነሳሳት እንደሚፈጥር አስገንዝበዋል።ሌሎች ዪኒቨርሲቲዎች ይህንን ፈለግ እንዲከተሉ እንደሚያነቃቃም እንዲሁ።
ፌስቲቫሉ ያለምንም ስጋት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉም ተመላክቷል።
የውድድሩ እጣ ማውጣት ስነ ስርዓት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ፡ የባህልና ስፖርት ሚንስቴር ሚንስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት፡ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱና ሌሎችም የስፖርቱ ቤተሰቦች በታደሙበት ተከናውኗል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












