ሩሲያ በዩክሬን ላይ በፈጸመችው ጥቃት ቢያንስ 3 ሰዎች መሞታቸውን እና 54 ሰዎች መቁሰላቸው ተገለጸ።
ጥቃቶቹም የባቡር መሰረተ ልማት ላይ ያነጣጠሩ ሲሆን በዚህም የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ከማድረሱም ባሻገር ሙሉ የባቡር አገልግሎት ማቋረጡን የዩክሬን መንግስታዊ የባቡር ኦፕሬተር ገልጿል፡፡
ቢያንስ የ46 ባቡሮች መዘግየት ገጥሟቸው የነበረ ሲሆን ወደ ኦዲሳ እና ዲኒፕሮ ያሉ መንገዶች ተቋርጠዋል ተብሏል፡፡
የዩክሬኑ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር ኦሌክሲ ኩሌባ በበኩላቸው “ጠላት በዚህ ምሽት በተደረገ ግዙፍ የድሮን ጥቃት የባቡር መረብን የሚያንቀሳቅሱ ማከፋፈያ ጣቢያዎችን ለማሰናከል ሞክሯል።” ብለዋል፡፡
ዘገባው የቲአርቲ ነው
በ – ፍቅረሚካኤል ዘየደ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












