በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከሪያል ማድሪድ ኮንትራቱን ጨርሶ የተሰናበትው ቫስኬዝ ለጀርመኑ ክለብ ለመፈረም ከጫፍ ደርሷል።
የ34 አመቱ ተጫዋች ዝውውሩን ለማጠናቀቅ ወደ ጀርመን ያቀና ሲሆን፤ የህክምና ሂደቱን በአፋጣኝ ይጀምራል ተብሏል። ሉካስ ቫስኬዝ በሪያል ማድሪድ የታዳጊ ቡድን ውስጥ ያደገ ሲሆን፤ በአውሮፓውያኑ 2015 ወደ ዋናው ቡድን ካደገ በኋላ ለ12 አመት ሎስ ብላንኮዎቹን አገልግሏል።
ስፔናዊው ተጫዋች በተሰጥኦ የታደለ በመሆኑ ረጅም ርቀት ይጓዛል የሚል ግምት ቢሰጠውም በተደጋጋሚ የሚፈትነው ጉዳት የሚጠበቀውን ያህል ስኬታማ እንዳይሆን እንቅፋት ሆኖበት ቆይቷል።
ቫስኬዝ በክለቦች አለም ዋንጫ እስከ ሩብ ፍጻሜ በተጓዝዝው ማድሪድ የመሰለፍ ዕድል ተሰጥቶት የመጨረሻውን ጨዋታ በነጩ መለያ ማድረግ ችሏል። የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታውን ሳይጠበቅ በሆፈናይም የተሸነፈው የአሰልጣኝ ኤሪክ ቴንሃግ ሊቨርኩሰን፤ ሁለገቡን ቫስኬዝን በነጻ ማግኘቱ ስኬት ነው ተብሎለታል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












