አትዮ ቴሌኮም የ2018 በጀት ዓመት እቅድና የቀጣይ ሦስት ዓመት አዲስ ስትራቴጂን በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬ ህይወት ታምሩ፤ በሰጡት መግለጫ ተቋሙ በ2018 በጀት ዓመትና ቀጣይ ሶስት ዓመታት ባለው ጊዜ የቴክኖሎጂ ፉክክሩን በልጦ ለመገኘት በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።
ኢትዩ ቴሌኮም ከሀገር ውስጥ ገበያው ባሻገር በዓለም ገበያ በውድድር ለመቅረብ ማቀዱን ዋና ስራ እፈጻሚዋ በመግለጫቸው አብራርተዋል። ተቋሙ ”ኔክስት ሆራይዘን” በተሰኘው አዲስ የእቅድ ስትራቴጂው፤ ሰው ተኮር የሆኑ ስራዎችን በስፋት ለማከናወን ማቀዱን ገልጿል።

ስትራቴጂው በቀጣይ ምዕራፍ ተቋማት በቴክኖሎጂ ተደግፈው የሥራ ቅልጥፍናን እና ውጤታማነትን እንዲያረጋግጡ ለማስቻል ያለሙ እቅዶችን ያካተተ መሆኑንም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬ ህይወት ተናግረዋል።
ኩባንያው በ2018 በጀት ዓመት የደንበኞችን ቁጥር ከ 83 ነጥብ 2 ሚሊዮን ወደ 88 ሚሊዮን ለማሳደግ ማቀዱንም አስታውቋል። በተጨማሪም 1ሺ 1መቶ 28 የሞባይል ጣቢያዎችን ለመገንባት ማቀዱን እና በዚህም የሞባይል ጠቃሚዎችን ቁጥር ወደ 11ሺ 238 እንደሚያሳድግ ገልጿል።
እንዲሁም በ3መቶ 22 የገጠር ቀበሌዎች የኔትወርክ ማስፋፊያ እንደሚያደርግ በመግለጫው ተመላክቷል። እንዲሁም 1ሺ 1መቶ 12 ሞባየል ጣቢያዎች በፋይበር እንዲገናኙ በበጀት ዓመቱ ይሰራል ብሏል ተቋሙ። ተቋሙ በቀጣይ በጀት ዓመት በ5መቶ 50 ከተሞች የ4ጂ እንዲሁም በ 10 ከተሞች የ5ጂ ማስፋፊያ እንደሚያደርግ አሳውቋል።

በአጠቃላይ በ2018 በጀት ዓመትና በቀጣይ ሶስት ዓመታት የእቅድ ስትራቴጂ ኢትዮ ቴሌኮም በኢትዮጵያም ሆነ ከኢትዮጵያ ባሻገር ትርጉም ያለው ለውጥ ለማምጣት እንደሚሰራ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬ ህይወት ታምሩ ገልጸዋል።
በ- ሰላማዊት ወንድወሰን












