ሰርቢያዊው አንጋፋ ተጫዋች ከፈረንሳዩ ክለብ ሊዮን ጋር የነበረውን ውል አጠናቆ ወደ ጣሊያኑ ሳሱኡሉ መጓዙን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
የ37 አመቱ ኒማኒያ ማቲች ለ18 ወራት በነበረው የሊዮን ቆይታ 55 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ መጫወቱ ተዘግቧል። ሳስኡሎ ባሳለፍነው የውድድር አመት በሴሪ ቢ ያሳለፈ ሲሆን፤ በሴሪ ኤ ለመቆየት የሚያስችሉትን ዝውውሮች በመፈጸም ላይ ይገኛል።
የቀድሞው የቼልሲ፣ ማንችስተር ዩናይትድ እና ሊዮን ተጫዋች ኒማኒያ ማቲች በሴሬው ከዚህ ቀደም ለሮማ መጫወቱ የሚዘነጋ አይደለም። የአንጋፋ ተጫዋቾች መሰባሰቢያ የሆነው ሴሪ ኤው በያዝነው የዝውውር ገበያ የ40 አመቱ ሉካ ሞድሪች፣ የ38 አመቱ ኦሊቨርን ጅሩድ እና የ34 አመቱ ኬቨን ዴብሯይነ ተቀላቅለውታል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












