የጣሊያኑ ክለብ ኤሲ ሚላን በግራ የተከላካይ መስመር ያለበትን ክፍተት ለመሙላት ኢስቱፒኒያንን ለማስፈረም መስማማቱን ዘ አትሌቲክ አስነብቧል።
ሚላን ከሳምንታት በፊት በስፍራው ላይ የሚጫወትለትን ቲዮ ሄርናንዴዝ ወደ ሳዑዲ አረቢያ መሸኘቱ ይታወሳል። ብራይተን ለኮሎምቢያዊው ተከላካይ 19 ሚሊዮን ፓውንድ ያስከፈለ ሲሆን፣ተጫዋቹ የጤና ምርመር ለማድረግ ወደ ጣሊያን ተጉዟል።
ኢስቱፒንያን በሚላን ቤት የሚያቆየውን የረጅም አመት ውል ይፈርማል ተብሎም ይጠበቃል። ውጤታማውን ማሲሚሊያኖ አሌግሪን በአሰልጣኝነት የቀጡሩት ሚላኖች በቀጣይ በአማካኝ እና የአጥቂ መስመር ተጫዋች ያስፈርማሉ ተብሎ ይገመታል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












