በ “ኮስቢ ሾው” ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ ላይ “ቴዎ ሃክስታብል” በተሰኘው ገጸ ባህርይ በመጫወት ትወናን በልጅነቱ የተቀላቀለው ማልኮም ጀማል ዋርነር በ 54 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
ዋርነር እሁድ በሊሞን ግዛት ውስጥ በምትገኘው “ኮክለስ” ከተማ በ “ፕላያ ግራንዴ” ባህር ዳርቻ ውስጥ እየዋኘ በነበረበት አጋጣሚ ነው ሰምጦ ህይወቱ ሊያልፍ የቻለው፡፡ አብረውት የነበሩት ሚስቱ እና ሴት ልጁ ግን ተርፈዋል።
የግዛቱ ባለሥልጣናት እንደተናገሩት፣ በአካባቢው የነበሩ ሰዎች የዋርነርን ህይወት ለመታደግ ወደ ባህር ዳርቻ ማውጣት ቢችሉም፣ ነገር ግን በአካባቢው ወደሚገኘው ቀይ መስቀል ከደረሰ በኋላ ህይወቱ አልፏል።
ዋርነር ከተወነባቸው ፊልሞች መካከል “The Father Clements Story” ፣ “Mothers Day” ፣ “Drop Zone” ፣ “Tyson”፣ “Fool’s Gold” ፣ “MegaChurch Murderer” ይገኙበታል፡፡
ቢቢሲ እንዳስነበበው
በሔርሜላ ተመስገን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












