የባየር ሊቨርኩሰኑ አማካኝ በያዝነው የተጫዋቾች የዝውውር ገበያ ከሰንደርላንድ ጋር ስሙ በስፋት ተያይዞ እየተዘገበ ይገኛል።
በተጠናቀቀው የውድድር አመት ወደ ፕሪምየር ሊግ ያደገው ሰንደርላንድ፣የፕሪምየር ሊግ ልምድ ያለውን አማካኝ ለማስፈረም ውይይት ላይ እንደሚገኝ ዘ አትሌቲክ አስነብቧል። የ32 አመቱ ዣካ በሰሜን ለንደኑ አርሰናል 7 አመት መቆየቱ ይታወሳል።
ስዊዘርላንዳዊው ተጫዋች ወደ ፕሪምየር ሊግ ዳግም መመለስ የፈለገ ሲሆን ሰንደርላንድን መቀላቀል እንደሚፈልግ ለጀርመኑ ክለብ ባለስልጣናት መናገሩ ተገልጿል። በአሰልጣኝ ሬጂስ ለብሪስ የቡድን ስብስብ ልምድ ያላቸው ተጫዋቾች ጉድለት በመኖሩ፣የዣካ መምጣት የማይቀር ነው ተብሏል።
ሰንደርላንድ በዝውውር መስኮቱ እስካሁን 5 ተጫዋቾችን አስፈርሟል። በአማካኝ መስመር ሃቢብ ዲያራ፣በክንፍ ሲሞን አዲንግራ እና ሸምሰዲን ታላቢ፣በመስመር ተከላካይነት ሪኔልዶን እና ኖሃ ሳዲቅን የግሉ አድርጓል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












