በክለቦች አለም ዋንጫ ፓልሜራስን በማሸነፍ ወደ ፍጻሜ የደረሰው ቼልሲ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የመክፈቻ ቀን ጨዋታው የሚደረግበት ቀን ይሸጋሸግልኝ ሲል ጥያቄ አቅርቧል።
የሊጉ አክሲዮን ማህበር የሰማያዊዎቹን ጥያቄ ውድቅ ያደረገው ሲሆን የምዕራብ ለንደኑ ክለብ በተያዘለት መርሃ ግብር መሰረት እንዲጓዝ ፈርዶበታል። ቼልሲ የፊታችን እሑድ ከፒኤስጂ ጋር የፍጻሜ ጨዋታውን ካከናወነ በኋላ የመጀመሪያ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ጨዋታውን ለማድረግ የአንድ ወር ጊዜ ብቻ ይቀረዋል።
አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ ቡድኑን ለቅድመ ውድድር ዘመን ለማዘጋጀት በቂ ጊዜ እንደማይኖር በማመናቸው ለሊጉ አወዳዳሪ አካል ቀድም ብለውም የመርሃ ግብር ማሻሻያ እንዲደረግ ሲጠይቁ ቆይተዋል።
የማንችስተር ሲቲውም አሰልጣኝ ጋርዲዮላ በተመሳሳይ ቅሬታቸውን ቢያሰሙም፣ሊጉ ቀደም ብሎ ለአመታት እንደሚያደርገው የመርሃ ግብር ሽግሽግ አላደርግም ብሏል። ቼልሲ በመጀመሪያ ሳምንት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታው በሜዳው ክሪስታል ፓላስን የሚያስተናግድ ይሆናል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












