በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰው አልባ የጦር አውሮፕላኖች በኪዬቭ ሰማይ ስር ጥቃት ካደረሱ በኋላ ተከታዩ ዕለት ማምሻውንም ዩክሬን ሰላም አላደረችም፡፡
የሰዎች ሕይወት አልፏል በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎችም ቆስለዋል የኪዬቭ ከተማም በጭስ ታውዳለች፡፡ የሀገሪቱ ዜጎችም በመኖርያ ቤታቸው እና በየመጠለያ ጣብያዎች ውስጥ እንቅልፍ አልባ ሌሊቶችን ማሳለፋቸው ተነግሯል፡፡
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ በቴሌግራም ገጻቸው እንዳስታወቁት ሞስኮ በኪዬቭ ላይ 400 ሰው አልባ የጦር አውሮፕላኖችን 18 ሚሳይሎችን 8 ባለስቲክ ሚሳይሎችን እና 6 ክሩዝ ሚሳይሎችን ተጠቅማ ጥቃት ፈጽማብናለች ብለዋል፡፡
ሩሲያ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ አድርጋው በማታውቀው ልክ 728 ድሮኖችን እና 13 ሚሳይሎችን በመጠቀም ጥቃት ያደረሰች ሲሆን የዩክሬን አየር ኃይል ግማሽ ያህሉን መመከት እንደቻለ አስታውቋል፡፡
ዘገባው የሲ ኤን ኤን ነው፡፡
በ-ፍቅረሚካኤል ዘየደ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












