የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ሃማስ ትጥቅ እስከፈታ ድረስ ለዘላቂ ተኩስ አቁም በራችን ክፍት ነው አሉ።
ሃማስ የቤኒያሚን ኔታንያሁን ሀሳብ የማይጨበጥ ነው በሚል አጣጥሎታል። ኔታንያሁ ሃማስ የአስተዳዳሪነት ሚና እንዳይኖረው እና ትጥቅ እንዲፈታ ማድረግ የእስራኤል መሰረታዊ ሁኔታዎች ናቸው ብለዋል።
በሰላም ማሳካት ከተቻለ እጅጉን መልካም ነው ያሉት ኔታንያ፣ በድርድር በ60 ቀናቱ ውስጥ ካልሆነ በሌላ መንገድ እናሳካዋለን በሚል አረጋግጠዋል። በሀይል ማለትም በጀግናው ጦራችን ዓላማችን ይሳካል በሚል ወታደራዊ አማራጩን አስቀምጠዋል።
ኔታንያሁ ሙሉ ለሙሉ ሃማስን የማጥፋት ውጥናቸውን በድጋሜ ማሳወቃቸው የአሜሪካውን የተኩስ አቁም እቅድ ጫና ውስጥ ያስገባዋል፡፡ የጋዛው ሃማስም ቢሆን በቀላሉ ራሱን ለእስራኤል ጦር አሳልፎ እንደማይሰጥ አረጋግጧል።
በዶሃ ኳታር የሚደረገው ድርድር በኔታንያሁ ሀሳብ ምክንያት እንዳይበተንም ስጋት ተደቅኗል፡፡
አልጀዚራ እንዳስነበበው፡፡
በ-ቢኒያም ካሴ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












