የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት፣ ብርን ወደ ሩብል አሊያም፤ ሩብልን ወደ ብር መመንዘር የሚቻልበትን አገልግሎት መጀመሩን አስታውቋል።
እንደባንኩ መረጃ አገላለጽ፣ ለ100 የኢትዮጵያ ብር 57.5872 ሩብል ወይም ለ1 ብር 0.575872 ሩብል የምንዛሬ ተመን አስቀምጧለሰ ነው የተባለው። ለኢትዮጵያ ብር ምንዛሬ ተመን የኮድ ቁጥር 230 የሰጠ ሲሆን በየዕለቱም የምንዛሬ ተመኑን የሚያሳውቅ ይሆናል።
ኢትዮጵያን ጨምሮ የ12 ሀገራት ገንዘቦች ከሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ ጋር ያላቸውን ይፋዊ የምንዛሪ ተመን ለማስቀመጥ ውሳኔ ላይ መድረሱን ከቀናት በፊት ማስታወቁ ይታወሳል።
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












