
:: :: :: :: :: :: :: :: ::
የቼልሲው ስፔናዊ ግብ ጠባቂ በተጠናቀቀው የውድድር አመት በውሰት ውል በቦርንመዝ ማሳለፉ ይታወሳል።
የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ተጫዋቹን በክለቡ ማቆየት ስለማይፈልግ ለለንደን ተቀናቃኙ አርሰናል ለመሸጥ ተስማምቷል።
መድፈኞቹ የ30 አመቱን ግብ ጠባቂ በ5 ሚሊዮን ፓውንድ የውል ማፍረሻ ሂሳብ የግላቸው ማድረጋቸውን አረጋግጠዋል።
ኬፓ አሪዛባላጋ በአውሮፓውያኑ 2018 ከአትሌቲክ ቢልባኦ ቼልሲን በ72 ሚሊዮን ፓውንድ የተቀላቀለ ሲሆን፣እስካሁንም ድረስ የአለማችን ውዱ ግብ ጠባቂ ነው።
በሰማያዊዎቹ ቤት ቆይታው 163 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ በመጫወት የ4 ዋንጫዎች አሸናፊ መሆን ችሏል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












