የምዕራብ ለንደኑ ክለብ በክረምት አዲስ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም እንደሚፈልግ እና የመጀመሪያ ምርጫው የሚላኑ ሜጋን መሆኑ ታውቋል።
ፈረንሳዊው ማይክ ሜጋን አዲስ ውልን በተመለከተ ለወራት ከክለቡ ጋር በመወያየት ላይ ሲሆን እስካሁን ስምምነት ላይ አለመድረሳቸው ታውቋል።
ቼልሲ በ30 አመቱ ግብ ጣባቂ ላይ ከፍተኛ ፍላጎት ያሳየ ሲሆን፣ከሚላን ባለስልጣናት ጋር የተጫዋቹን ዝውውር በተመለከተ ውይይት ማድረግ መጀመራቸው ተገልጿል።

በተያያዘ ዜና ውሃ ሰማያዊዎቹ ከማንችስተር ዩናይትድ በውሰት ውል አምጥተውት የነበረውን ጄደን ሳንቾ ወደ እናት ክለቡ መልሰውታል።
ቼልሲ ተጫዋቹን በ25 ሚሊዮን ፓውንድ በቋሚነት የመውሰድ ዕድሉን ሊጠቀም ባለመፈለጉ፣ ስምምነታቸውን የሚቀድበት 5 ሚሊዮን ፓውንድ ለቀያይ ሰይጣኖቹ ከፍሏል።
እንግሊዛዊው ሳንቾ በቼሲ ባደረገው የአንድ አመት ቆይታ በተሰለፈባቸው 42 ጨዋታዎች 5 ጎል ሲያስቆጥር 10 ወደ ግብ የተለወጡ ኩሶች ማቀበል ችሏል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












