። ። ። ። ። ። ። ። ።
በጋዛ የሚገኘው የጤና ሚኒስቴር እንደገለጸው ከ2023 ጀምሮ 117 ሺህ ፍልስጤማውያን በጦርነቱ ምክንያት መቁሰላቸው ሲገለጽ የሟቾች ቁጥር ከ51 ሺህ ተሻግሯል፡፡
ባለፉት 24 ሰዓታት እስራኤል በጋዛ ባደረሰችው የአየር ላይ ጥቃት 39 ፍልስጤማውያን ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን፣ የቆሰሉትን ወደ ሆስፒታል ማድረስ እና ሕክምና መስጠትም ፈታኝ መሆኑን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው፡፡
የእስራኤል ጦር በጋዛ ሰርጥ በመስፈሩ በየጊዜው ጥቃቶች መድረሳቸውም ቀጥሏል ተብሏል፡፡
የዓለም ዓቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በበኩሉ በጋዛ በደረሰው ቀውስ ምክንያት ለጥፋቱ ተጠያቂ ናቸው ያላቸውን የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና የቀድሞ መከላከያ ሚኒስትሩ ዮአቭ ጋላንት ላይ የእስር ማዘዣ ወጥቶባቸው እንደነበር ዘገባው አስታውሷል፡፡
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእርዳት እና ሥራዎች ኤጀንሲ በበኩሉ በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲደረግ መጠየቁን አልጄዚራ ዘግቧል፡፡
በ- ፍቅረሚካኤል ዘየደ












