። ። ። ። ። ። ። ። ።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዩክሬን እና ሩሲያ ነጋችንን የሚያጠናክረውን የቢዝነስ ስምምነት ለመፈራረም ዝግጁ ሆነዋል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ተንታኞች በበኩላቸው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስልጣን በያዝኩ በ24 ሰዓታት ውስጥ ጦርነቱን አስቆመዋለሁ ማለታቸውን በማንሳት ቃላቸውን አልጠበቁም ጦርነቱም አልቆመም ሲሉ በተደጋጋሚ እየተቿቸው ነው፡፡
አሜሪካ ግን የ30 ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነትን በእቅድ መልኩ አቅርባ የነበረ ሲሆን ዩክሬን ብትቀበለውም በሩሲያ በኩል ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱ ይታወሳል፡፡
ትራምፕም በበኩላቸው በኪዬቭ እና በሞስኮ መካከል የሚደረገው ውይይት እና ድርድር ፍሬ አልባ ከሆነ አሜሪካ ከአሸማጋይነት ትወጣለች ሲሉ ተናግረዋል፡፡
የቢዝነስ ስምምነት ያደርጋሉ ከሚል ውጪ ዝርዝር ማብራሪያ አልተገለጸም፡፡ ዘገባው የዩሮሜድያን ነው፡፡
በ-ፍቅረሚካኤል ዘየደ












