::::::::::::::::::::::::::::::::::
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ተጠሪ ተቋማት እና የብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው።
ጉብኝቱ በከተማዋ የተከናወኑ እና በመከናወን ላይ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎችን፣ የመልሶ ማልማትና የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ ሌሎች በርካታ የልማት ሥራዎችን ያካተተ መሆኑ ተጠቁሟል።

በአዲስ አበባ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች ለነዋሪዎች ምቹ አካባቢ የሚፈጥሩና የከተማዋን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት በእጅጉ የሚያሳድጉ መሆናቸውም ተገልጿል።

በተጨማሪም የልማት ሥራዎቹ አዲስ አበባን የተቀናጀ የመሠረተ ልማት የተሟላላት ከተማ እንድትሆን የሚያስችሉ ናቸው መባሉን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።
በከተማዋ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የዓድዋ ድል መታሰቢያ፣ የአዲስ ዓለም ዓቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል፣ የነገዋ የሴቶች ተሐድሶ ማዕከል፣ የተለያዩ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች እንዲሁም ሌሎች በርካታ የልማት ስራዎች መከናወናቸው ይታወቃል።












