የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎን አልመው እየተጫወቱ የሚገኙት ሁለቱ ቡድኖች ዛሬ ምሽት ኢቲሀድ ላይ ይጫወታሉ።
የአምናው ባለክብር የፔፕ ቡድን በ58 ነጥብ በደረጃ ሰንጠረዡ 4ኛ ላይ ያለፉ አምስት ጨዋታዎችን በሙሉ በአሸናፊነት ያጠናቀቀው የኡናይ ኤምሪ ቪላ ደግሞ በአንድ ነጥብ ዝቅ ብሎ 7ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠው ይገናኛሉ።
የፕሪሚየር ሊጉ ከፍተኛ አምስት ክለቦች በሚቀጥለው የውድድር ዘመን በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የሚሳተፉ ሲሆን ጠንካራ ፉክክር እያደረጉ ካሉት ሊቨርፑልና አርሰናል ቀጥሎ የሚገኙት አምስት ክለቦች በአንድ ነጥብ ብቻ የሚለያዩበት አስደናቂ ውድድር እየተካሄደ ነው።
ኖቲንግሃም ፎረስት በ60 ፣ ኒውካስል በ59 እና ሲቲ በ 58 ከ3-5 ሲቀመጡ ቼልሲና ቪላ ዕኩል 57 ነጥብ ሰብስበዋል።
የሲቲው አሰልጣኝ ጋርዲዮላ “ቪላዎች የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎን ለማግኘት ጠንካራ ተፎካካሪዎች ናቸው” ብለዋል።
“ከጓደኛዬ ሉዊስ ኤንሪኬ ቡድን ፒኤስጂ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ አይቼ በጣም ተደንቄያለሁ እነርሱ ወደ ኋላ አፈግፍጎ በመጫወት የተዋጣላቸውና በማይታመን ሁኔታ በደንብ የተደራጁ ናቸው” ብለዋል።
“ጨዋታው የፍጻሜ ነው እና ደጋፊዎቻችንን እንፈልጋለን ከመጀመሪያው ደቂቃ ጀምሮ ሊረዱን እንደሚችሉ ተስፋ አደርጋለሁ” ሲሉ አክለዋል።
በ- ይበልጣል ሰውነት












