NBC Ethiopia ሊያ ክብሮም
April 21, 2025

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ በ88 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸዉን ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል። በቫቲካን ካሣ ሳንታ ማርታ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ህይወታቸዉ ማለፉም ነዉ የተነገረዉ። ፍራንሲስ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በመገኘት በሺዎች ለሚቆጠሩ ምእመናን “እንኳን ለፋሲካ በዓል በሰላም አደረሳችሁ” መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ ነዉ ህይወታቸው ያለፈው።ዘገባዉ የቢቢሲ ነዉ












