:::::::::::::::::::::::::::::::::::
ትላንት ምሽት ማንችስተር ሲቲ እና ኒውካስትል ዩናይትድ ድል ማድረጋቸውን ተከትሎ 4ተኛ ደረጃውን የተቀማው ቼልሲ ወደ ቻምቲዮንስ ሊግ ስፍራ ለመመለስ ማሸነፍ የግድ የለዋል።
ምን ጊዜም ውጥረት በማያጣው የሁለቱ ክለቦች ግንኑነት። ያለፉት 5 ጨዋታዎች በሰማያዊዎቹ የበላይነት ተጠናቋል። ቼልሲ በ4ቱ ጨዋታ ድል ሲያደርግ፣ስፐርስ በ1ዱ አሸንፏል።
የአሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ ቼልሲ በቀሪ ጨዋታዎች ነጥብ በመሰብሰብ የቻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎን ማረጋገጥ አላማው ሲያደርግ፣ በሊጉ ከወገብ በታች የሚገኘው ስፐርስ ደረጃውን ከማሻሻል በዘለለ ወደ አውሮፓ ውድድር ወደሚያስገባው ስፍራ ለመመለስ አዳጋች ይሆንበታል።
በውድድር አመቱ መጨረሻ ሊሰናበቱ ይችላሉ የሚባሉት አሰልጥኝ አንጅ ፖስቴኮግሉ ክለቡ በይሮፓ ሊግ በሚኖረው ውጤት መነሻነት ቆይታቸውን እንደሚወስን ይጠበቃል።
ለምሽቱ ጨዋታ ቼልሲ ከጉዳት ያገገሙትን ኮል ፓልመርን፣ ኒኮላስ ጃክሰን እና ኖኒ ማድዌኬን በቡድን ስበስቡ አካትቷል።
በቶተንሃም በኩል ሚኪ ቫን ደቭን እና ፔድሮ ፖሮ በተከላካይ መስመር መጣመራቸው በጎ ዜና ሲሆን ዴያን ክሉሰቭስኪ በጉዳት ከስብስብ ውጪ ተደርጓል።
ብራዚላዊው ሪቻርልሰን ወደልምምድ መመለሱን ያነሱት ፖስቴኮግሉ አካላዊ ዝግጁነቱ ገና በመሆኑ ለምሽቱ ጨዋታ አይደርስም ብለዋል። ጨዋታው 4 ሰዓት ሲል በስታንፎርድ ብሪጅ ይጀምራል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












