::::::::::::::::::::::
በሚያናማር በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሟቾች ቁጥር 3085 መድረሱ ተገለጸ፡፡
ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ በተከሰተው እና 7 ነጥብ 7 በሪኪተር ስኬል የተመዘገበው ርዕደ መሬት፤ የሟቾችን ቁጥር ከፍ ሊያደርገው እንደሚችል ስጋት መኖሩን ወታደራዊ ጁንታው አስታውቋል፡፡
በሚናማር በደረሰው አደጋ ከማቾች በተጨማሪ 4,715 መቁሰላቸው እና 341 ሰዎች መጥፋታቸው ይፋ ተደርጓል፡፡

በሀገሪቱ ሁለተኛዋ ግዙፍ ከተማ በሆነችው ሰሜናዊ ማንዳላ እንዲሁም በሌሎች ግዛቶች የተከሰተው ርዕደ መሬት መሰረተ ልማችን ከጥቅም እንዳደረጋቸውም እየተነገረ ነው፡፡
ወደ ታይላንድም የተሻገረው የርዕደ መሬት አደጋ፤ የ22 ሰዎችን ህይወት ቀጥፎ 35 የሚሆኑትን ደግሞ አቁስሏል ፡፡ ዘገባው የኤቢሲ ኒውስ ነው፡፡
በ-ቶማይ መኮንን












