፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 7 የለውጥ ዓመታት የተመዘገቡ ውጤቶችን የሚያሳይ የፎቶ አውደ ርዕይ በኦሮሞ ባህል ማዕከል ተከፈተ።

በዐውደ ርዕዩ መክፈቻ ላይ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)፥የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ሰዓዳ አብዱራህማን፣የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ እና ሌሎች የፌዴራልና የክልሉ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

ዐውደ ርዕዩ ላይ ባለፉት ሰባት የለውጥ ዓመታት አጠቃላይ የፖለቲካ፣ የሰላም፣የልማትና መልካም አስተዳደር ጉዞ እና የተገኙ ስኬቶች የሚታዩበት መሆኑም ተመልክቷል።












