ሁለቱ ክለቦች በዘንድሮው አመት በተለያዩ የውድድር ምዕራፎች ለ4ተኛ ጊዜ ይገናኙበታል።
በውድድር አመቱ መጨረሻ ከሚላን እንደሚለያዩ የሚጠበቁት አሰልጣኝ ሰርጂዮ ኮንሴሳአ ለምሽቱ ጨዋታ ከፍተኛ ግምት ማስጠታቸው ተነግሯል።
በሴሬኣው 9ኛ ስፍራ ላይ የሚገኘው ሚላን አስቸጋሪ የውድድር ዘመን እያሳለፈ ነው። ባሳለፍነው እሁድ በናፖሊ ከተሸነፉ በኋላ የቻምፒዮንስ ሊግ ስፍራን ይዞ የማጠናቀቅ ተስፋቸው አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል።
በወቅታዊ አቋም የተሻለ ሁኔታ ላይ የሚገኘው ኢንተር ሴሪዓውን በ3 ነጥብ ልዩነት በመምራት ላይ ይገኛል።
በቀጣይ ሳምንት ከባየርን ሙኒክ ወሳኝ የቻምፒዮንስ ሊግ ፍልሚያ ያለባቸው ኢንተሮች፣ ከከተማ ተቀናቃኛቸው ፈተና ይጠብቃቸዋል።
ጨዋታው ምሽት 4 ሰዓት ኢል በሳን ሲሮ ይጀምራል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












