በፈረንጆች ሚያዚያ 9 ሁለቱ ወገኖች በዶሃ ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት እንደሚነጋገሩ ታውቋል።
በምስራቃዊ የኮንጎ ግዛት በስፋት የሚንቀሳቀሰው ኤም 23 በርካታ ስፍራዎችን ከመንግስት ጦር አስለቅቆ በእጁ አስገብቷል።
በአገሪቱ የሚደረገው የርስበርስ ጦርነት ከኤም 23 በተጨማሪ ከሌሎች ታጣቂ ቡድኖች ጋርም የሚደረግ በመሆኑ መንግስታዊ የዕለት ከዕለት ስራዎችን ለመስራት አዳጋች አድርጎታል።
ከዚህ ቀደም የኤም 23 እና የመንግስት ተወካዮችን በአንጎላ ለማደራደር ታስቦ የነበረ ቢሆንም ኤም 23 አመራሮቼ “የአውሮፓ ሕብረት ማዕቀብ አለባቸው” በማለት በስፍራው አልተገኘም።
እስካሳለፍነው ወር ኪንሻሳ ከአማጺያን ጋር አልወያይም ብትልም፣ፕሬዚዳንት ፍሊክስ ሺሲኬዲ በዶሃ ቆይታቸው ከሩዋንዳው ፖል ካጋሜ መገናኘታቸው ለሰላማዊ ንግግር ያላቸውን ፍላጎት አመላካች ነው ተብሏል።
ሩዋንዳ በኮንጎ የውስጥ ፖለቲካ እጇን በማስገባት እና አማጺያንን በመርዳት ስትወነጀል በተደጋጋሚ ታይቷል።
በ- አልፈሪድ ነስሮ












