፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ህዳር 30 2017| NBC ETHIOPIA- ለካሳንችስ ልማት ተነሺዎች በገላን ጉራ የተገነባነው የገላን ጉራ የመኖሪያ እና የተቀናጀ ልማት መንደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ መርቀው ክፍት አድርገዋል።
ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት የሆነው የገላን ጉራ የመኖሪያ እና የተቀናጀ የልማት መንደር በውስጡ መኖሪያ ቤቶች ፣ትምህርት ቤቶች ፣የአስፋልት መንገድ፣ የምገባ ማዕከል ፣የዳቦ ፋብሪካ እና የእንጀራ መጋገሪያ ማዕከል፣ደረጃውን የጠበቀ የህጻናት መጫወቻ እና የህጻናት ማቆያ ብሎም የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ ይገኙበታል ። እነዚህ የልማት ስራዎች አዲስ አበባን ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የተያዘው እቅድ አንዱ ማሳያ መሆኑ ተመላክቷል።



የገላን ጉራ የመኖሪያ እና የተቀናጀ የልማት መንደር በውስጡ 6500 ነዎሪዎችን የያዙ 1200 መኖሪያ ቤቶች ፣በ2 ወር ጊዜ ዉስጥ ግንባታቸው የተጠናቀቁ ከቅድም አንደኛ ደረጃ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ያሉ ትምህርት ቤቶች ከነምገባ ማዕከሉ የያዙ ፣ 1.6 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለዉ የአስፋልት መንገድ እንዲሁም ከ20 በላይ አውቶቡሶችን በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚያስችል ተርሚናል ያካተተ መሆኑ ተገልጿል ።በተጨማሪም ለ270 እናቶች የስራ እድል መፍጠር የሚያችሉ እንጀራ መጋገርያ ፋብሪካ አለው። በቀን 60 ሺህ ዳቦ የማምረት አቅም ያለው የዳቦ ፋብሪካ እና የእህል ወፍጮዎችን ይዟል።
በ-ሰላማዊት ወልደገሪማ












