
በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ባቲ ወረዳ ጫካ ገብተው የህዝብን ሰላም ሲያውኩ የነበሩ በርካታ የሸኔ ታጣቂዎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ለኮማንዶ ክፍለ ጦር እጅ ሰጥተዋል።
በአካባቢው ተሰማርቶ ግዳጁን ሲወጣና ከማህበረሰቡ ጋር ስለሰላም ወይይት ሲያደርግ የቆየው የኮማንዶ ክፍለጦር ምክትል አዛዥ ለውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ሌተናል ኮሎኔል ወርቁ አደሪ እንዳሉት የሸኔ ታጣቂዎች የተለያዩ ዓይነት በርካታ መሳሪያዎችን እና ቦንቦችን እንዲሁም ትጥቆችን ይዘው በሰላም እጅ ሰጥተዋል።
በዚህም፡
የሰላም ጥሪውን የተቀበሉ የሸኔ አባላት ብዛት =105
ይዘውት የገቡ መሳሪያ ብዛት = 45
ያለመሳሪያ የገቡ ( ጀሌ ) ብዛት = 60
የብትን ጥይት ብዛት = 1,425
ቦንብ ብዛት = 26 እና ሌሎች ትጥቆችም ይገኙበታል።
በግዳጅ ቀጠናው የተሰማራው ሻለቃ አዛዥ ሻምበል ስሜ ዘለቀ እጅ የሰጡ ሸኔዎች ካለፈው ስህተታቸው ተምረው ዛሬ ወደ ማህበረሰቡ እንደመጡ ሁሉ ነገም ከህዝብ ጋር የልማት ስራዎችን ሰርተው ሀገርን ማሳደግ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋቸዋል።
ምንጭ፡ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት











