Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Analysis

የኢትዮጵያን እጣፋንታ የሚወስነው ቀይ ባህር

የኢትዮጵያን እጣፋንታ የሚወስነው ቀይ ባህር

November 16, 2026
in Analysis, International, Politics
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ከንግድና ከኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ባለፈ፣ ከሀገሪቱ የወደፊት ዕድገትና ከቀጠናው ጂኦፖለቲካዊ ሁኔታ ጋር የተያያዘ ጉዳይ እንደሆነ ይገለጻል። የሀገሪቱ የወደብ አገልግሎት ወጪ፣ የሕዝብ ቁጥር ዕድገትና በቀጠናው ያለው የፖለቲካ ፍጥጫ የባህር በር ጥያቄውን አስፈላጊነት የሚያጎሉ ጉዳዮች መሆናቸው ይነገራል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፉ ግንኙነት መምህር እንዲሁም በNBC ኢትዮጵያ የ“ዓለም አቀፍ” ፕሮግራም ተባባሪ አዘጋጅ የሆኑት ትዕዛዙ መሐመድ፣ ኢትዮጵያ ካለችበት ነባራዊ የኢኮኖሚና የጂኦፖለቲካ ሁኔታ አንጻር የባህር በር እንዲኖራት የምታቀርበው ጥያቄ ተገቢ መሆኑን አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ ለወደብ አገልግሎት ብቻ በየዓመቱ ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ እያወጣች መሆኑን ያነሱት መምህር ትዕዛዙ፣ ይህ ገንዘብ ለሌሎች የልማት ዘርፎች ቢውል በርካታ የሀገሪቱን የመሰረተ ልማት ችግሮች መፍታት እንደሚችል አንስተዋል። አያያዘውም የሀገሪቱ ኢኮኖሚ እያደገ ሲሄድ የወደብ አገልግሎት ወጪውም በእጥፍ ሊጨምር እንደሚችል በማስረዳት፣ ይህም ሀገሪቱ ላይ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫና እንደሚያመጣ አመልክተዋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥርና ኢኮኖሚ በፍጥነት እያደገ መምጣቱን በመጠቆም፣ ይህንን እያደገ የመጣውን የሕዝብና ኢኮኖሚያዊ ለዉጥ ከቀይ ባህር ጋር ማሰተሳሰር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።በቀጠናው ያለውን የፖለቲካ ተፅዕኖና የሀገራት ግንኙነት በተመለከተም፣ ግብጽ በኢትዮጵያ ጎረቤት ሀገራት ውስጥ ያላትን አሉታዊ ጫና በማሳደግ የኢትዮጵያን የውሃ ጥቅሞችና ሉዓላዊነት ለማደናቀፍ እየሰራች መሆኑን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል የኤርትራ አመራሮች ከኢትዮጵያ ጋር የኢኮኖሚ ትብብር ከመፍጠር መራቃቸው ለሁለቱም ሀገራት የማይጠቅም መሆኑን አንስተው፣ ሱዳንም የግብጽን ጥቅም ብቻ ከማስቀደም ይልቅ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የጋራ ጥቅም ማጠናከር እንዳለባት ነው ያስታወሱት።

እንደአብነት የቀድሞውን የሱዳን መሪ ኦማር አልበሽር አስተዳደርን ያነሱት ተባባሪ አዘጋጁ፣ በወቅቱ ከኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የናይል ወንዝ ፍሰትንና ከጎርፍ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በጋራ ለመፍታት ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር ጠቅሰው፣ ሆኖም በግብጽ ግፊትና ተጽዕኖ ምክንያት የትብብር ሂደቱ መስተጓጎሉን ይጠቅሳሉ።

በአባይ ወንዝ ዙሪያ የግብጽን አቋም መምህሩ ሲገልፁ፣ ግብጽ ከዓመታት በፊት ከነበረው “አባይ የእኔ ስጦታ ነው” ከሚል ያለፈበት አስተሳሰብ ወጥታ ዘመኑን የዋጀ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በመከተል የውሃ ፍላጎቷን በአማራጭ ማሟላት እንደምትችል አንስተዋል። እስካሁን ድረስም በቅኝ ግዛት ጊዜ የተደረጉ ኢፍትሃዊ ውሎችን ብቻ በመያዝ የላይኛው ተፋሰስ ሀገራትን በአባይ ወንዝ ላይ ያለእኔ ፍቃድ ምንም ነገር ማድረግ አትችሉም ማለቷ አግባብ እንዳልሆነ ተናግረዋል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ የህዳሴውን ግድብ ስትገነባ የውሃ ፍሰቱን ሙሉ በሙሉ እንዳላቋረጠች እና የጋራ ተጠቃሚነትን እንደምትፈልግም ነው ያነሱት።

የአጎራባች ሀገራትን ትብብር አስፈላጊነት በተመለከተ፣ የኢትዮጵያና የኤርትራ ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት የተሳሰረ እንደመሆኑ መጠን በትብብር መስራት በንግድና በኢኮኖሚው ዘርፍ ትልቅ ዕድገት ማምጣት እንደሚቻል ተናግረዋል።

ከዚህ አኳያ የኤርትራ አመራሮች ከኢትዮጵያ ጋር አብሮ ለመስራት ፈቃደኛ አለመሆናቸው ለሀገሪቱና ለሕዝቧ ጉዳት እያስከተለ መሆኑን አንስተዋል።

በታሪክ ውስጥ ዓለም አቀፍ ድንበሮች በጦርነትም ሆነ በዲፕሎማሲ ስምምነት ሊለወጡ እንደሚችሉ ያስረዱት መምህሩ፣ የፈረንሳይን አልሳስና ሎሬን ግዛቶች እንዲሁም የሆንግኮንግን ታሪክ እንደምሳሌ ጠቅሰዋል። ፈረንሳይ በጦርነት ያጣቻቸውን አልሳስና ሎሬን ከአንደኛው ዓለም ጦርነት በኋላ ማስመለሷን፣ ሆንግኮንግም ከረጅም የብሪታንያ ቆይታ በኋላ ለቻይና መመለሷን በማስታወስ፣ የግዛት ጉዳዮች በዲፕሎማሲያዊ መንገድ መፍትሔ ሊያገኙ እንደሚችሉ አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ ያላግባብ ያጣችውን የባህር በር በፍትሐዊና በሰላማዊ መንገድ ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት በዲፕሎማሲያዊ መንገድ መቀጠል እንዳለባት ገልጸው፣ ይህም የሀገሪቱን ሉዓላዊ ጥቅምና የኢኮኖሚ ፍላጎት ከቀጠናዊ ትብብር እንዲሁም ከጋራ ተጠቃሚነት ጋር ባገናዘበ መልኩ መከናወን እንዳለበት ተናግረዋል።

በ-በረከት አስረስ

Source: @NBCEthiopia
Via: NBCEthiopia
Tags: EgyptEthiopiairanIsraelNIle RiverREd SeaRussiaRussia Ukraine wartrump
ShareTweetShare
Previous Post

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Next Post

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

Related Posts

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ
#ethiopia

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
8
“የኤርትራ ሕዝብ ከኢሳያስ በላይ ጠላት የለውም” – አቶ ጌታቸው ረዳ
Analysis

“የኤርትራ ሕዝብ ከኢሳያስ በላይ ጠላት የለውም” – አቶ ጌታቸው ረዳ

November 16, 2026
20
ምርኮኞቹ ጀነራሎች ያጋለጡት የህወሓት ሴራ
Analysis

ምርኮኞቹ ጀነራሎች ያጋለጡት የህወሓት ሴራ

November 14, 2026
57
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
50
ብሔራዊ ጥቅም ማለት መንግስትን መደገፍ አይደለም!
Analysis

ሚዲያዎችና ብሄራዊ ጥቅም

November 11, 2026
21
ብሔራዊ ጥቅም ማለት መንግስትን መደገፍ አይደለም!
Analysis

ብሔራዊ ጥቅም ማለት መንግስትን መደገፍ አይደለም!

November 11, 2026
24
Next Post
የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው" - ጌታቸው ረዳ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?