። ። ። ። ። ። ። ። ። ። ። ። ። ።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቻይና ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንና ሺ ጂንፒንግ ጋር በሚቀጥለው ሳምንት እንገናኛን አሉ።
ስለኑክሌር ጦር መሳሪያና የኢራን ጦርነት እንመክራለን ያሉት ትራምፕ ከሁለቱ ሀገራት ፕሬዚዳንቶች ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ አንድ ላይ ለመነጋገር እድሉ ይፈጠራል ሲሉ አረጋግጠዋል።
ትራምፕ መሪዎቹን በተናጠል ከዚህ ቀደም በተለያየ አጋጣሚ እንዳገኟቸው የሚዘነጋ አይደለም።
ከፈረንጆቹ ህዳር 18 እስከ 19 በሸንጀን ቻይና በሚደረገው የኤዥያ -ፓስፊክ የኢኮኖሚ ትብብር ፎረም ላይ የሶስትዮሽ ድርድሩ ይጠበቃል።
የመሪዎቹ በአንድ መድረክ ላይ መምከር
ለበርካታ ዓለም አቀፍ ችግሮች መፍትሔ ያመጣል የሚል ተስፋም ተጥሎበታል።
ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከትራምፕ ጋር በስልክ ሲወያዩ የዩክሬን ጉዳይንም ለመቋጨት መነሻ የሚሆናቸውን ሀሳብ ማቅረባቸው አይዘነጋም።
ቮሎድሜር ዘለንሰኪ ዩክሬን በሌለችበት መድረክ ላይ የሚደረግ ውይይት አደገኛ ሊሆን እንደሚችልም በተደጋጋሚ ያስጠነቅቃሉ።
የቻይናው ሺ ጂንፒንግ የዚህን ዓመት ጉባዔ ሲያስተናግዱ በርካታ ጉዳዮችን ታሳቢ ያደርጋሉ፤ለድርድርም ጠረጴዛ ላይ የተለያዩ ሀሳቦችን ያቀርባሉ።
አሜሪካ እና ሩሲያ የባለ21 ሀገራቱ የኤዥያ -ፓስፊክ የኢኮኖሚ ትብብር ፎረም (APEC) ዓባል ሀገራት መሆናቸው ይታወቃል።
አውስትራሊያ፣ጃፓን፣ማሌዥያ ፣ፊሊፒንስ እና ሲንጋፖርም ዓባላት ናቸው፤ በግዙፉ መድረክ ላይም ተሳታፊ ይሆናሉ።
አልጀዚራ እንዳስነበበው።
በ-ቢኒያም ካሴ
። ። ።
ማስፈንጠሪያውን (ሊንኩን) በመጫን NBC ኢትዮጵያን ይጎብኙ ይወዳጁ
https://linktr.ee/NBCEthiopiaTV
#NBCEthiopia
#ሆኖ_መገኘት
#Ethiopia












