ኢትዮጵያ 2ኛውን የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ በአህጉሪቷ መዲና አዲስ አበባ ለማስተናገድ ዝግጅቷን አጠናቃለች።
በፓን-አፍሪካኒዝም መንፈስ የሚካሄደው ይህ ታላቅ ጉባኤ፣ በርካታ የአህጉሪቱን ገዥና ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎች በአንድ ዙሪያ የሚያሰባስብ ነው።
ጉባኤው ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለችውን ሁለንተናዊ የከፍታ ጉዞ፣ ሀገራዊ እውነታዎችና የልማት ስራዎችን ለአህጉሩ መሪዎች በግንባር ለማስረዳት ሰፊ እድል ይፈጥራል።
በተጨማሪም ከሀገራቱ ጋር የሚደረገውን የፓርቲ ለፓርቲ እና የመንግስት ለመንግስት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግረዋል ተብሎ ይጠበቃል።

Source:
@NBCETHIOPIA
Via:
NBC Ethiopia












