Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

ሰላም ለፍጥረት ሁሉ አስፈላጊ ነው – ፓስተር አዳነ ደቻሳ

ሰላም ለፍጥረት ሁሉ አስፈላጊ ነው - ፓስተር አዳነ ደቻሳ

October 29, 2026
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

NBC Ethiopia

ኤንቢሲ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በሚያዘጋጀው “የኤዲተሮች ጠረጴዛ” መርሃ ግብር የተገኙት የግጭት መከላከልና የሠላም ግንባታ ከፍተኛ ባለሞያ ፓስተር አዳነ ደቻሳ በሃገራችን አሁናዊ የግጭት ሂደትና በሃገር በቀል እሴቶች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል::

በኢትዮጵያ ለዘመናት ተጠብቀው የቆዩ ባህላዊና ሀገር በቀል የግጭት አፈታት ከዘመናዊ ፍርድ ቤቶች ይልቅ የዕለት ተዕለት ማህበራዊና ቤተሰባዊ አለመግባባቶችን በስፋት በመፍታት ረገድ ጉልህ ሚና ሲኖራቸው፣ ፍርድ ቤቶች ህግ እና መረጃ ላይ ተመስርተው አሸናፊና ተሸናፊን በመለየት ውሳኔ ሲሰጡ ሀገር በቀል የሽምግልና ስርአቶች ግን የተቀየሙ ወገኖችን በማስታረቅና የተበላሸውን ማህበራዊ ትስስር መልሶ በመገንባት ዘላቂ አብሮነትን ያረጋግጣሉ በማለት ገልጸዋል::

በየክልሉ የሚዲያ ኮሚኒኬሽን በመኖሩ የክልል ሚዲያዎች ባህላዊ የእርቅ ስርአቶችን ለማስተዋወቅ የጀመሯቸው በጎ ጥረቶች ስለግጭት አፈታት አልፎም ውጤታማነቱን የሚገልፅ ሲሆን፣ የሃይማኖት ሚዲያም ይህን ምሳሌ በመውሰድ ለሰላም ሥራ ጉልህ ሚና መጫወት እንደሚችል አመላክተዋል።

በሀገራችን ያሉ የባህላዊ ግጭት አፈታቶች መካከል የኦሮሞ ማኅበረሰብ የገዳ ሥርዓት በአባገዳዎች መሪነት ከባድ የደም መፋሰስን ጭምር በዕርቅ የሚፈታ ሲሆን፣ በአማራና በተለያዩ አካባቢዎች የሚሠራበት የሽምግልና ሥርዓት ደግሞ በተከበሩ ሽማግሌዎች አማካኝነት እርቅ ያወርዳል። በተጨማሪም የጋሞ ማኅበረሰብ የሸንጎ አውድ የሆነው ዱቡሻ፣ የሲዳማው አፊኒ እና የአኙዋክ ብሔረሰብ ዊርኩር ግጭቶችን ለመፍታትና ፍትሕን ለማስፈን የሚያገለግሉ ጠንካራ ማኅበረሰባዊ ተቋማት ሲሆኑ ጥንታዊ አሠራሮች የሀገሪቱን የበለጸገ ባህላዊ የሰላም ግንባታ ቅርስ ያሳያሉ።

አሁንም የሽምግልና ስርአቶቹን ህግጋትና ስነ-ምግባር በጥልቀት በመመርመር ረገድ ትልቅ ክፍተት እንዳለ በመግለጽ፣ አክለውም እነዚህ ሀገር በቀል እሴቶች ያልተማሩ ሰዎች ድርጊት ተደርገው ሳይናቁ በበቂ ዝግጅትና ሽፋን ለህብረተሰቡ ሊቀርቡ እንደሚገባና ይህም ለሰላም ግንባታው ሂደት ትልቅ ግብዓት እንደሚሆን አመላክተዋል።

​በሌላ በኩል በዲጂታል ዘመን በማህበራዊ ሚዲያ አማካይነት የሚሰራጩ የሐሰት መረጃዎችና የጥላቻ ንግግሮች ለሰላም ግንባታው ስራ ትልቅ ተግዳሮት መሆናቸውን በተለይም በግለሰቦች መካከል የሚፈጠሩ ተራ አለመግባባቶችን የብሔር ወይም የሃይማኖት መልክ በመስጠት የሚሰራጩ የሀሰት ዜናዎች ሰላምን በከፍተኛ ደረጃ የሚያደፈርሱ በመሆናቸው ህብረተሰቡም ሆነ የሃይማኖት አባቶች እንዲህ ያሉ እኩይ ድርጊቶችን በጋራ ሊያወግዙና ሊገስጹ እንደሚገባ አሳስበዋል።

​በመጨረሻም ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የመንግስት፣ የሃይማኖት ተቋማት፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የመገናኛ ብዙሃን የተቀናጀና የተናበበ ርብርብ ማድረግ እንዳለባቸው እና ግጭት ከመከሰቱ በፊት ቅድመ የመከላከል ስራዎችን መስራት በየቦታው ያሉ በጎ ማህበራዊ እሴቶችን ማጎልበት እና ሰላም ለሰው ልጅ ብቻ ሳይሆን ለፍጥረት ሁሉ አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት ሁሉም አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል::

በ – የአብሥራ ተፈራ

Source: @NBCETHIOPIA ​
Via: @NBCETHIOPIA ​
Tags: #addisababaEthiopiaFacebookMeta
ShareTweetShare
Previous Post

”የአፍሪካ ዘመን አሁን ነው”

Next Post

ኢህአዴግ ታሪካዊ ስህተት ሰርቷል !- የቀድሞ የአሰብ ምክትል አስተዳዳሪ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
8
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
15
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
51
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
ኢህአዴግ ታሪካዊ ስህተት ሰርቷል !- የቀድሞ የአሰብ ምክትል አስተዳዳሪ

ኢህአዴግ ታሪካዊ ስህተት ሰርቷል !- የቀድሞ የአሰብ ምክትል አስተዳዳሪ

ህወሃት ክንፉ ተሰብሯል!-ጀነራል ባጫ ደበሌ

ህወሃት ክንፉ ተሰብሯል!-ጀነራል ባጫ ደበሌ

የመካከለኛው ምስራቅ እጣ ፈንታ

የመካከለኛው ምስራቅ እጣ ፈንታ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?