
የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅት ምክር ቤት 7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁን አስመልክቶ የምስጋናና የእውቅና ምሽቱን ያዘጋጀውን መድረክ እያካሄደ ነው።
በዚሁ መድረክ የተገኙት የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ታዬ ምርጫ ሚሊዮኖች በንቃት ተሳትፈዋል ። ሚሊዮኖች በነቂስ በማለዳና በውድቅት ለሊት ወጥተው የመረጡት ሰላምን አማራጭ በማድረጋቸው ነው ብለዋል።
እኛ አንዳንድ አለም አቀፍ ሚዲያዎች እንደሚዘግቡት ግጭት ሳይሆን ሰላም ነው አማራጫችን ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።
አዘውትረው በክፉ ለሚያዩን አካላት እልፍ አዕላፍ ወጥተው ስልጣን በምርጫ ብቻ እንደሚገኝ ወጥተው በመምረጥ አሳይተዋል ብለዋል።
ምርጫው ያሳየን ሀገር ፖለቲካ የሚመራው በስሜታዊነት ሳይሆን በእውቀት፣በስክነት መሆኑን አሳይቷል ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።
የምርጫው አሸናፊ የድል ሳይሆን የኃላፊት፣የህዝብን የልብትርታና የህዝብን ህሊና የራስ ሀብት የማድረግ ኃላፊነት ነው ብለዋል።
የሚገዳደሩ ኃይሎችን ማረም እና መረቅም ሌላው የአሸናፊው ፓርቲ ቀጣይ ስራ መሆኑን ጠቁመዋል።
በሚሊዮን ሊመርጥ የወጣው ህዝብ ኋላቀሮችን በኃይልና በነውጥ ስልጣንና ሰላም እንደማይመጣ በካርዱ አሳይቷል ብለዋል።
ሕዝቡ በምርጫው እንዳይሳተፍ በፀረሰላም ኃይሎች እየተዛተባቸው በቁርጠኝነት ድምፅ ሰጥተዋል ብለዋል።
ለዚህም ፕሬዝዳንት ታዬ ህዝቡ በረጅም ሰልፎች ውስጥ ድምፁን ሰጥቷል። ለዚህም ህዝቡ ምስጋናና አድናቆት ይገበዋል ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ በታዛቢነት ለተገኙት ለኢጋድ፣የአፍሪካ ሕብረት፣ ለፀጥታና ደህንነት ተቋማት፣ ለምርጫ ቦርድ፣ ለሚዲያ ተቋማትና የሲቪህ ማህበራት ለምርጫው ስኬት ላደረጉት የጋራ የትብብር አመስግነዋል።
በመድረኩ የኢፌዲሪ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሞዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንዔል ክብረት፣ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፣ የሕ/ተ/ም/ቤት አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮች ተገኝተዋል።
በ-እየሩሳሌም ዓለሙ












