Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

የምስራቅ አፍሪካን ዘላቂ ሰላምና ዕድገት ለማፋጠን የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ትብብር ማጎልበት ያስፈልጋል

የምስራቅ አፍሪካን ዘላቂ ሰላምና ዕድገት ለማፋጠን የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ትብብር ማጎልበት ያስፈልጋል

May 18, 2026
in News, Politics
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

የምስራቅ አፍሪካን ዘላቂ ሰላምና ዕድገት ለማፋጠን የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ትብብር ማጎልበት እንደሚያስፈልግ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ገለጹ።

በሶማሌ ክልል ርዕሰ መዲና ጅግጅጋ ከተማ በቀጣናው ሰላም እና ደኅንነት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ከፍተኛ ቀጣናዊ ፎረም እየተካሄደ ይገኛል።

’’ቀጣናዊ ተቋማትን ማጠናከር ለአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀው ፎረም ቀጣናዊ መፍትሄዎች ለቀጣናዊ ችግሮች የሚለውን ዕሳቤ ማስተዋወቅ ዋና ዓላማው አድርጓል።

ይህ መድረክ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት፣ በሰላም እና ፖለቲካዊ ምክክር ማዕከል፣ በሶማሌ ክልል መንግስትና ሌሎች አጋር አካላት በጋራ ተዘጋጅቷል።

በጅግጅጋው ከተማ በተዘጋጀው ፎረም ላይ የኢትዮጵያን ጨምሮ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት መንግስታት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ምሁራን፣ ባለድርሻ አካላትና ተጋባዠ እንግዶች ታድመዋል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በፎረሙ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ፎረሙ የጋራ ዓላማን በማሳካት ሰላማዊና የተረጋጋ መፃኢ ጊዜን ለመቅረፅ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

የአፍሪካ ቀንድ በዓለም ላይ ካሉ እጅግ አስፈላጊ ቀጣናዎች አንዱ ነው ያሉት አፈ ጉባኤ ታገሰ፤ ቀጣናውም የአህጉራት የገበያና ባህል ስትራቴጂካዊ ጥቅሞች ድልድይ ነው ብለዋል።

የምስራቅ አፍሪካ ቀጣና መልክ ዓምድራዊ አቀማመጥና የህዝቦች ብዝኃ ትስስርም ከታሪኩ ጋር ተዳምሮ አስፈላጊነቱን እንዲጎላ ማድረጉን አስረድተዋል።

በሁሉም መለኪያ ወርቃማ ፀጋ የታደለው ቀጣናም ግጭት፣ አለመተማመን፣ መፈናቀል፣ የፖለቲካ ደካማነት፣ የሰብዓዊ መብት ጫና እና የውጭ ተፅዕኖ መታየት እንደሌለበት አብራርተዋል።

የአፍሪካ ቀንድ በችግርና ቀውስ መነጽር የሚታይበት አካሄድም ቀጣናውን ከትብብር ይልቅ የፉክክር መንደር ተደርጎ እንዲሳል ማድረጉን አንስተዋል።

ይህ መለወጥ አለበት ያሉት አፈ ጉባኤው፤ የአፍሪካ ቀንድ የወደፊት ዕጣ ፋንታም በራስ አቅም እንጂ በውጭ አካላት ሊጻፍ እንደማይገባ አስገንዝበዋል።

በዚህም የቀጣናውን ሀገራት ልማት፣ ሰላምና ደኅንነት ለማጠናከር የተቋማት፣ የማህበረሰቡ፣ የምሁራን፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ሴቶችና ወጣቶችን ትብብር ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አፅንኦት ሰጥተዋል።

ቀጣናዊ ወኪልነትን ለማረጋገጥም በራስ ማሰብ፣ መፍትሔ መፈለግ፣ አጋርነትን ማጠናከር፣ የዕርስ በዕርስ ትብብርና የጋራ ዕድሎችን በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ዜጎች መቀረፅ እንዳለበት ገልጸዋል።

የምስራቅ አፍሪካ አጋሮችም ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ቀጣናዊ የልማት፣ ክብርና ሉዓላዊነት፣ ሰላምና ደኅንነትን የሚያረጋግጥ ድጋፍ ማድረግ እንደሚኖርባቸው ተናግረዋል።

ዘላቂ ሰላም በምኞት ብቻ አይገነባም ያሉት አፈ ጉባኤ ታገሰ፤ ሰላም የሚገነባውም በጠንካራ ተቋማት፣ በፍትሐዊና አካታች ትብብርና የፖለቲካ አጋርነት እንዲሁም በማይቋረጥ ውይይት ነው ብለዋል።

ሰላም በሕዝብ አመኔታና በተጠያቂ ተቋማት ላይ ሊመሠረት እንደሚገባ አፅንኦት የሰጡት አፈ ጉባዔው፤ ኢትዮጵያ ሰላማዊ፣ የተረጋጋና የተባበረ የአፍሪካ ቀንድ እንዲኖር ጥልቅ ፍላጎት እንዳላት አስገንዝበዋል።

የኢትጵያ ሰላም፣ ልማት፣ ትብብርና ቀጣናዊ ተሳተፎም ከጎረቤት ሀገራት ጋር የተሳሰረ መሆኑን አስረድተዋል።

በዚህም የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ትብብርን በማጠናከር ሰላም ልማትና ብልፅግናቸውን ለማረጋገጥ በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ አጋርነትን ማጎልበት እንዳለባቸው አንስተዋል።

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ፤ የሶማሌ ክልላዊ መንግስት ይህንን የጂግጂጋ ፎረም በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ብልጽግናን ለማስፈን የሚያስችሉ መንገዶችን ለመቀየስ የሚረዳ ስልታዊ የውይይት መድረክ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቀዋል።

ለረጅም ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ በጣም ደህንነቱ ያልተጠበቀ አካባቢ ተደርጎ ይቆጠር የነበረው ክልል ዛሬ ተለውጦ እንዲህ አይነት ዓለም አቀፋዊ የውይይት እና የሰላም ፎረም ማስተናገዱ ራሱ የሚሰጠው ተምሳሌትነት እጅግ የላቀ ትርጉም አለው ሲሉ ገልጸዋል።

ይህ ታላቅ ውይይት በጂግጂጋ ከተማ መካሄዱ ልዩ ትርጉም እንዳለውም ጠቁመዋል፡፡

Tags: EthiopiaIGAD
ShareTweetShare
Previous Post

መረጃ ሀገረ መንግሥት ለመገንባት ቁልፍ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Next Post

በፕሪሚየር ሊጉ ምርጡ የበላይነት ጊዜ የየትኛው ክለብ ነው?

Related Posts

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ
#ethiopia

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
11
የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
የኢትዮጵያን እጣፋንታ የሚወስነው ቀይ ባህር
Analysis

የኢትዮጵያን እጣፋንታ የሚወስነው ቀይ ባህር

November 16, 2026
10
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
“የኤርትራ ሕዝብ ከኢሳያስ በላይ ጠላት የለውም” – አቶ ጌታቸው ረዳ
Analysis

“የኤርትራ ሕዝብ ከኢሳያስ በላይ ጠላት የለውም” – አቶ ጌታቸው ረዳ

November 16, 2026
20
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
Next Post
በፕሪሚየር ሊጉ ምርጡ የበላይነት ጊዜ የየትኛው ክለብ ነው?

በፕሪሚየር ሊጉ ምርጡ የበላይነት ጊዜ የየትኛው ክለብ ነው?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የግራንዴር ሴራሚክ ፋብሪካ መርቀው አገልግሎት አስጀመሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የግራንዴር ሴራሚክ ፋብሪካ መርቀው አገልግሎት አስጀመሩ

እኔ በማውቀው መጠን በምንም መንገድ ትብብር ከምርጫው አይወጣም!

እኔ በማውቀው መጠን በምንም መንገድ ትብብር ከምርጫው አይወጣም!

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?