Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home Economy

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቃና ቴሌቪዥን ጋር ያደረጉት ቆይታ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቃና ቴሌቪዥን ጋር ያደረጉት ቆይታ

March 25, 2026
in Economy, News, Politics
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቃና ቴሌቪዥን ጋር ቆይታ ያደረጉ ሲሆን በቆይታቸውም ወደ ኤሌክትሪክ መኪናዎች ስለሚደረገው ሽግግር፣ ስለኮሪደር እና ወንዝ ዳርቻ ልማቶች ድርብርብ ዓላማዎች እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች ማብራርያ ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ መኪናዎችን  በስፋት ጥቅም ላይ ለማዋል የጀመረችው እንቅስቃሴ የረጅም ጊዜ የኃይል ዋስትና ለማረጋገጥ ያለመ ስትራቴጂካዊ ውሳኔ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የነዳጅ መኪናዎችን አጠቃቀም ለመቀነስ የተያዘው አቅጣጫ መጀመሪያ ላይ ቅሬታዎች ቢነሱበትም፣ ዓለም አቀፋዊ የነዳጅ ዋጋ መዋዥቅና የጂኦፖለቲካዊ ግጭቶች በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድሩትን ተፅዕኖ ለመቋቋም ብቸኛው አማራጭ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ነዳጅ አምራች ሀገር አለመሆኗን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የነዳጅ ዋጋ በጨመረ ቁጥር የሚከሰተውን የዋጋ ንረት ለመቆጣጠር በሀገር ውስጥ የሚመረተውን የታዳሽ ኃይል መጠቀም የኃይል ሉዓላዊነትን እንደሚያረጋግጥ አብራርተዋል።  

“በዋጋ ደረጃ የነዳጅና የኤሌክትሪክ ወጪ እኩል ቢሆን እንኳ፣ የኤሌክትሪክ መኪና ተመራጭ ነው፤ ምክንያቱም ኃይሉን እዚሁ ሀገር ውስጥ ስለምናመርት እንደ ነዳጅ ‘ተዘጋብኝ’ የሚል ስጋት አይኖርም” በማለት የችግሩን አሳሳቢነትና የመፍትሔውን አስፈላጊነት አስገንዝበዋል።

ወደ ኤሌክትሪክ መኪና የሚደረገው ሽግግር ከወጪ ንግድ የሚገኘውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ለነዳጅ ግዢ ከመስጠት የሚታደግ ከመሆኑም ባለፈ፣ ለአካባቢ ጥበቃና ለዜጎች የኑሮ ጫና መቀነስ ትልቅ ፋይዳ አለው ብለዋል።

መኪናዎቹ ጪስና ድምፅ የሌላቸው መሆኑ እንዲሁም የማንቀሳቀሻ ወጪያቸው እጅግ አነስተኛ መሆኑ ለሀገርም ሆነ ለተጠቃሚው ትልቅ ዕድል መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቃለ መጠይቃቸው የኮሪደር ልማትንም ያነሱ ሲሆን የከተማን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ የነዋሪዎችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ድርብርብ ዓላማ ያለው ግዙፍ ስትራቴጂካዊ ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል።

ማንኛውም የልማት ሥራ ግልጽ ግብ ሊኖረው እንደሚገባ በመጥቀስ፣ የኮሪደር ልማት ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና አካባቢያዊ ግቦችን በአንድነት አቀናጅቶ የያዘ መሆኑን አብራርተዋል።

ፕሮጀክቱ በግንባታ ወቅትና ከግንባታ በኋላ ተከታታይነት ያለው የሥራ ዕድል ከመፍጠሩም በላይ፣ ለወጣት መሐንዲሶች ትልቅ የተግባር ልምድ መጋሪያ ሆኖ ማገልገሉን ተናግረዋል።

በዩኒቨርሲቲ ከሚገኘው የንድፈ-ሐሳብ እውቀት ባለፈ ወጣቶች ከፍተኛ የተግባራዊ እውቀት እንዲቀስሙ ማስቻሉን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በአዲስ አበባ ልምድ ያገኙ ወጣቶች አሁን ላይ በክልል ከተሞች አስገራሚ የዲዛይንና የግንባታ ሥራዎችን እያከናወኑ እንደሚገኙም ጠቁመዋል።

የኮሪደር ልማቱ አንዱ አካል የሆነው የቤት ግንባታ፣ በሀገሪቱ የነበረውን የቤት እጥረት ለመቅረፍ በከፍተኛ ፍጥነት በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶችን ለመገንባት ማስቻሉን አንስተዋል።

ልማቱ ይዞታዎችን በመለየትና ለተገቢው ዓላማ በማዋል፣ ለኑሮ የማይመቹና በላስቲክ የተሠሩ ቤቶች በዘመናዊና ደረጃቸውን በጠበቁ ሕንፃዎች እንዲተኩ እያደረገ መሆኑም አብራርተዋል።

በተጨማሪም የመንገድ፣ የመብራትና የእግረኛ መንገዶች መሻሻል በኮሪደሩ አቅራቢያ ያሉ የቤትና የሕንፃ ዋጋዎች እጅግ እንዲጨምሩ በማድረጉ፣ ባለሀብቶች በልበ ሙሉነት በዘርፉ ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል ብለዋል።

ልማቱ አማራጭ መንገዶችን በመፍጠርና የነበሩትን በማስፋት፣ ቀደም ሲል የነበረውን የትራፊክ መጨናነቅ በከፍተኛ ደረጃ መቅረፉን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በአዲስ አበባ የመኪናና የእግረኛ መንገዶች ተለይተው በመሠራታቸው፣ ነዋሪዎች ሳይጉላሉ በፈጠነ ጊዜ ወደሚፈልጉት ቦታ መድረስ እንዲችሉ ማድረጉንም ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ያልተገዛችና የታላቅ ድል ባለቤት ብትሆንም፣ የውጭ ሀገር መሪዎች ወደ ሀገራችን ሲመጡ በክብር የአበባ ጉንጉን የሚያስቀምጡበት በቂ ስፍራ እንዳልነበረም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለጹ ሲሆን፣ እንደ ዓድዋ ድል መታሰቢያ እና የታደሱት ቤተ-መንግሥታት ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ይህንን ታሪካዊ ክፍተት በመሙላት የሀገሪቱን ገጽታ መቀየራቸውን ጠቁመዋል።

እነዚህ የልማት ሥራዎች ቱሪዝምን ከመሳብ ባለፈ፣ ትውልዱ የሀገሩን ማንነት አውቆ በኢትዮጵያዊነቱ እንዲኮራና የአርበኝነት ስሜቱ እንዲገነባ ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገንዝበዋል።

አዲስ አበባ እንደ ኒውዮርክ፣ ፓሪስ እና ሪዮ ዲጄኔሮ ከተሞች የራሷ የሆኑ ዓለም አቀፍ መለያዎች ሊኖሯት እንደሚገባ በመጥቀስ፣ በእንጦጦና በየካ አካባቢ የተሰሩ ስራዎች ከተማዋን እንደ “ሆሊውድ” ያሉ ዓለም አቀፍ የቱሪስት መስህቦች ባለቤት እንደሚያደርጓት አመልክተዋል።

ይህ ከተማን ዘመናዊ የማድረግ ሥራ የኢትዮጵያ የክብር ታሪክ ለዓለም በሚመጥን መልኩ ለማሳየት ያለመ መሆኑንም ገልፀዋል።

የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ ለማሳካት የሚከናወኑ የልማት ሥራዎች በትውልድ መስዋዕትነት የሚገነቡና የዜጎችን የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቆይታቸው አንስተዋል።

እንደ ከተማ መልሶ ማልማትና ክላስተር እርሻ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ሲከናወኑ ለጊዜው የሚታዩ ተግዳሮቶች ለረጅም ጊዜ ስኬት ሲባል የሚታለፉ መሆናቸውን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የልማቱ ድምር ውጤት በሀገርም ሆነ በቤተሰብ ደረጃ ዕድገት እንጂ ውድቀት እንደማያመጣ አስረድተዋል።

የሀገር ግንባታ በዋዛ ፈዛዛ እንደማይሳካና የበለጸጉ ሀገራት ዛሬ ለደረሱበት ደረጃ የበቁት በዜጎቻቸው “ደም እና አጥንት” መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውሰው የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ ለማሳካት የሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ዋናው ዓላማ ለሕዝብና ለሀገር ብልጽግና መሥራት መሆኑን አስገንዝበዋል።

አሁን የሚታዩ ችግሮች ጊዜያዊ ቢሆኑም፣ በረጅም ጊዜ ሂደት ኢትዮጵያ ስታድግ የማይጠቀም ዜጋ እንደማይኖርና እያንዳንዷ ሰከንድ የኢትዮጵያን ብልጽግና በሚያረጋግጡ ጉዳዮች ላይ ብቻ እንደምትውል አረጋግጠዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወነ ያለው የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ለብዙ ሀገራት ምሳሌ የሚሆን፣ ለልጆቻችን የምናወርሰው ኩራት እና የነገዋ ኢትዮጵያ አዲስ መልክ ነው ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዘርፉ የተከናወነውን ልማት አብራርተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳመለከቱት፣ በአጠቃላይ 50 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው እና ስምንት ወንዞችን የሚያካትተው ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት ለከተማዋ አዲስ ገጽታ እያላበሰ የሚገኝ ሲሆን፣ ቀደም ሲል ለጤና አስጊ እና መርዛማ የነበሩ የወንዝ ዳርቻዎች በአሁኑ ወቅት ወደ ለምለም አረንጓዴ ስፍራዎች እና ማራኪ የመዝናኛ ቦታዎች ተቀይረዋል።

ይህ የልማት ሥራ የከተማዋን ነዋሪዎች የኑሮ ዘይቤ ከመቀየሩ ባለፈ፣ ጥቁር እና መርዛማ የነበሩ ወንዞችን በዘመናዊ መንገድ በማከም ንጹሕ ውኃ እንዲፈስባቸው አድርጓል።

በዚህም ተፈጥሮ ወደ ቀድሞ ይዘቷ እንድትመለስ የተደረገ ሲሆን፣ ከወንዞቹ የሚወጣው ቆሻሻም ተመልሶ ለማዳበሪያ እና ለሌሎች ጥቅሞች እንዲውል እየተደረገ ይገኛል።

በተጨማሪም በወንዝ ዳርቻዎቹ ሰፊ የመራመጃ መንገዶች እና የስፖርት ሜዳዎች በመገንባታቸው፣ ጤናማ እና አብሮነት የሰፈነበት ማኅበረሰብ ለመፍጠር ትልቅ ዕድል ተፈጥሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አክለውም፣ በአዲስ አበባ የተመዘገበው ይህ ስኬታማ የልማት ተሞክሮ በአሁኑ ወቅት በሐዋሳ፣ በቢሾፍቱ፣ በባሕር ዳር እና በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞችም ተግባራዊ መሆን መጀመሩን ገልጸዋል።

ይህ ተግባር ከተሞች ለነዋሪዎቻቸው ምቹ እንዲሆኑ እና የተፈጥሮ ሀብታቸውን ለልማት እንዲያውሉ የሚያስችል ትልቅ ሀገራዊ ንቅናቄ መሆኑንም ገልጸዋል።

Source: @NBCETHIOPIA
Via: NBC ETHIOPIA
Tags: Corridor deveopmentElectric VehicleEthiopiaPM Abiy Ahmed
ShareTweetShare
Previous Post

“ወላሂ ማርያምን እወዳታለሁ!” | ቆይታ ከገጣሚ ከድር አሊ ጋር | NBC ቅዳሜ

Next Post

“ይቻላል” የኪነጥበብ እና የምስጋና ምሽት ለሻለቃ አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ | NBC ቅዳሜ

Related Posts

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ
#ethiopia

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
8
የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
የኢትዮጵያን እጣፋንታ የሚወስነው ቀይ ባህር
Analysis

የኢትዮጵያን እጣፋንታ የሚወስነው ቀይ ባህር

November 16, 2026
9
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
8
“የኤርትራ ሕዝብ ከኢሳያስ በላይ ጠላት የለውም” – አቶ ጌታቸው ረዳ
Analysis

“የኤርትራ ሕዝብ ከኢሳያስ በላይ ጠላት የለውም” – አቶ ጌታቸው ረዳ

November 16, 2026
20
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
Next Post
“ይቻላል” የኪነጥበብ እና የምስጋና ምሽት ለሻለቃ አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ | NBC ቅዳሜ

"ይቻላል" የኪነጥበብ እና የምስጋና ምሽት ለሻለቃ አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ | NBC ቅዳሜ

ፖለቲካዊ ችግሮችን በጋራ እንፍታ የሚል የመሪ ጥሪ የታየበት የለውጡ ዘመን

ፖለቲካዊ ችግሮችን በጋራ እንፍታ የሚል የመሪ ጥሪ የታየበት የለውጡ ዘመን

ድርድር ወይንስ ጊዜ መግዣ? | ሁቲዎች በገልፉ ጦርነት…! _NBC አለም-አቀፍ

ድርድር ወይንስ ጊዜ መግዣ? | ሁቲዎች በገልፉ ጦርነት...! _NBC አለም-አቀፍ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?