February 23, 2026
በአማራና በትግራይ ክልላዊ መንግሥታት አከራካሪ የሆኑት ምርጫ ከልሎችን በተመለከተ የተሰጠን ውሣኔ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ7ተኛ ጠቅላላ ምርጫ የጊዜ ሠሌዳ ላይ በተመለከተው መሠረት ጥር 22 ቀን 2018 ዓ.ም. የመራጮች ምዝገባ ለማካሄድ እየተዘጋጀባቸው ያሉትን ምርጫ ከልሎችና ምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር ለሕዝብ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል።

ይህንኑ ቦርዱ ያወጣውን የምርጫ ከልሎችና ጣቢያዎች ዝርዝር ተከትሎ ጥር 25 ቀን 2018 ዓ.ም. የፌዴሬሽን ምክር ቤት በቁጥር ፌደም/አፈ/5/13138 ለቦርዱ በጻፈው ደብዳቤ በትግራይ እና በአማራ ከልላዊ መንግሥታት መካከል አከራካሪ ሆነው የቆዩት የአምስት ምርጫ ከልሎች የይገባኛል ጥያቄው እስከሚፈታ የሁመራ፣ የአዲረመፅ፣ የኮረም አፍላ፣ የጠለምትና የራያ አላማጣ ምርጫ ከልሎች ከትግራይ ከልላዊ መንግሥት ውጪ ሆነው ለብቻቸው በቀጥታ ለሕዝብ ተወካዮች ምከር ቤት ምርጫ እንዲደረግ ምከር ቤቱ መወሠኑን ለቦርዱ አሳውቋል፡፡

የከልል ምከር ቤት ምርጫው በአካባቢዎቹ ላይ የተነሣው የይገባኛል ውዝግብ በሕገ-መንግሥት ውሣኔ ሲፈታ አመቺ ጊዜ ተመርጦ ወደፊት እንዲካሄድ መወሠኑንም እንዲሁ ምከር ቤቱ አሳውቋል። በመሆኑም ቦርዱ በፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሣኔ መሠረት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ከላይ በተጠቀሰው አግባብ ለመፈጸም የሚያስችለውን ሕግና ሥርዓት በመጠበቅ ተግባራዊ የሚያደርግ መሆኑን ያስታውቃል።












